እስኪ ሀሳባቹን አካፍሉኝ። በጣም የምትወደኝ ልጅ አለች። ይሄን ከነገረችኝ እና ካወቅኩ 4 አመት አልፎታል። የዛኔ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ መግባት ስለማልፈልግ በግልፅ ግንኙነት ውስጥ መግባት እንደማልፈልግ ነገርኳት እሷም የኔን ፈላጎት ለመክበር ብቻ ብላ ተቀበለችኝ። ግን በዚህ አላበቃ ለወራትም ቢሆን እንቆይ እና ለሰላምታ ብለን በተደዋወልንበት እንደ አዲስ chat ማድረግ እንጀምራለን። ከዛም ማቆም እነዳለብን እነግራት እና መለያየቱ የስቃይ አለም ቢሆንባትም የምንለያየበት ምክንያት እሷም ስለምታምንበት እና እኔ ደስስ እንዲለኝ ብላ ትቀበላለች። ችግሩ እኔ ጭራሽ እንደማላቃት ሴት መለያየት አልፈልግም። በጣም አከብራታለው አዳንቃታለው ግን ደግሞ የወደፊት አጋሬ መሆንን ልቤ ሊቀበል አልቻለም። እሷ ቀን እና ሌሊቱን አብረን ብንሆን ደስተኛ ናት። ዛሬ እንጋባ ብላት አልቅሳ ትቀበለኛለች። ሁሉንም እያወቀች ማውራታችንን ትፈልገዋለች። " ደስስ የሚል ስቃይ ነው" ትለኛለች። ፈፅሞ በኔ ምክንያት እንድትጎዳ አልፈልግም። ግን ፈለገችውም አልፈለገችው እየጎዳኋት ነው። ብቻ ታሪኩ ረጅም ነው ለማሳጠር ሞክሪያለው። እስኪ ንገሩኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ችግሬ ምንድን ነው?
Feb 03, 2021Endesu khone betam kebade nw.....endena hasab esuwan lemweded mokrh kalchalk beka rakat becherash atgebuwa athune...akalhu endesuwa lante yemtasb aynet sw merak yekbdale gn abrehat mehone kalchalk rakat biyanse yane hememu bibertabatm yeshalale.......kalwededkat befsume lesuw blh abrehat endathone cuz legizaw yetkmkat bimeslhm kes bekes kante yemtfelgwn fkr selmatagne tegodalch
Feb 03, 2021