Is making out a sin? Please I need an explanation form my orthodox brothers and sisters
Feb 02, 2021መዳራትና ሥርዓተ ተክሊል በሥርዓተ ተክሊል ዙሪያ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል መዳራትን በተመለከተ የሚነሳው ዋነኛው ነው ብንል ሐሰተኛ የሚለን አይኖረም። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ መዳራት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ መመለስ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ። እንግዲ ከፈቀዳችሁልኝ መዳራትን ላብራራ መዳራት ምንድን ነው ? መዳራት የዝሙትና የአመንዝራነት መጀመሪያ ድርጊት (ዋዜማ) ነው ወንድና ሴት በፍትወት ተነድተው ሲጫወቱ ሲተሻሹ ሲሳሳሙ ከዚህም ያለፈ የዝሙት ስሜታቸውን የሚቀሰቅስ ተግባራት ሲያከናውኑ መዳራት ፈጸሙ ይባላል። መቼም ዛሬ ዛሬ ፍቅረኛ ሁኖ መሳሳም ከሌለ ፍቅር ሕይወት ውስጥ ያለን ሁሉ አይመስለንም። በየፊልሙ በቃረምነው የኃጢአት እውቀት የተነሳ እጮኝነት በተቀደሰ አግባብ ማስኬድ አቅቶን በዓለም ሐሳብ ስንንገዳገድ ማየት የተለመደ ከሆነ እኮ ሰነባብቷል እጮኛሞች ከሚገጥማቸው ፈተናዎች /ተግዳሮቶች/ መካከል የመዳራት ኃጢአትን ዋነኛው ነው። እጮኛሞች እየተላመዱና በጠለቀ ፍቅር ውስጥ እየገቡ ሲሄዱ ገለልተኛ ቦታ በመሄድ ለብቻ ሆኖ በመጫወት ለዚህ ፈተና ተጋላጭ የሚሆኑበት ክፍተት ለሰይጣን ይሰጡታል :: በእጮኝነት ወቅት ተገናኝቶ ማውራት የበለጠ መተዋወቅ በጣም አስፈላጊ እና ለነገው የትዳር ሕይወታቸው መሰረታዊ ቢሆንም ገለልተኛ እና ለዝሙት እና ለመዳራት የሚያጋልጥ ቦታዎች መቀጣጠር ግን እንደ ክርስቲያን ተገቢ ነገር አይደለም መዳራት ራሱን የቻለ ኃጢአት ነው። እግዚአብሔርን ያሳዝናል። በፍትዎት የሚያቀልጥ ነውና በዝሙት ሳይጥለን ላይለቀንም ይችላል። አንዳንድ ወጣቶች ከንፍር ለከንፍር መሳሳም ምን አለበት እያሉ ጥያቄ ሲጠይቁ እንሰማለን። ሲጀመር የአንዲት ሴት አካል የአንተ አካል ሊሆን የሚችለው ቤተ ክርስቲያን ባርካ ሚስት አድርጋ ስትሰጥህ ብቻ ነው። የራስህ አካል እስክትሆን ድረስ ጠብቀህ በሥርዓት የባልነት ሚናህን ትወጣለህ እንጂ ባልተፈቀደልህ አካል ላይ በፍትዎት የሚያቀልጥህን ተግባር እንድትፈጽም ቤተ ክርስትያን አትፈቅድልህም ካልሳምኩሽ የእኔ እና የአንቺ ግንኙነት ፍቅር ላይ የተመረኮዘ መሆኑን በምን አውቃለሁ አትበል ፍቅር የሚገለጠው በመሳሳም አይደለም በመሳሳም ቢሆንማ ይሁዳ በመሳም አሳልፎ ጌታው በ30 ባልሸጠው ነበር የተጫጩ ወንድና ሴት በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጋብቻ ሳይፈጸምላቸው ካህኑ ፈቅደውልን ነው። ተማምለን ቃል ተገባብተናል ልንጋባ የቀረን ጥቂት ቀን ወይም ትንሽ ነገር ብቻ ነው። የሚሉና ተቀባይነት የሌላቸው ሌሎች ምክንያቶች በመደርደር መዳራት ውስጥ መግባት አይገባቸውም ከዚህ በፊት በነበረው ስህተት በመዳራት ኃጢአት ውስጥ ያለፉ ማለት መሳሳም ፣ ከባድ የሆነ መላፋት ፣ በአንድ አልጋ ላይ በመተኛት መደበኛ የሆነው ዝሙት ከመስራት ውጭ ሌላውን ነገር ያደረጉ ክርስቲያኖች ተክሊልን በተመለከተ ምንም ሳይደብቁ ለንስሐ አባታቸው ሁኔታውን በማስረዳት ይፈቀድልኛል ወይስ አይፈቀድም ? የሚለውን ጥያቄ በመጠየቅ የንስሐ አባታቸው መልስ ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል ይህንን ጥያቄ ዝርዝር ጉዳዩን ከሰማ በኋላ የመወሰን መብት ያለው የንስሐ አባት ነው። ለንስሐ አባት በመዳራት የኃጢአት ቆይታችን የፈጸምነውን እርኩሰት ምንም ሳንደብቅ በሚገባ መናገር እንዳለብን በፍጹም መርሳት የለብንም #ምንጭ:- አቤል ተፈራ Comment @kokuha_haymanot_bot 💚 @kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Feb 02, 2021