ye like mezemran tewodros "mutan eyasnesu dwuyan fewesu smun bcha yzew tamene nigusu" yemilewen mezmur please lakulgn
Jan 19, 2021✞ብርና ወርቅ ሳይዙ✞ ብርና ወርቅ ሳይዙ ዓለማትን ዞሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ቃሉን እየዘሩ ሙታን እያስነሡ ድውያን ፈወሱ ስሙን ብቻ ይዘው(፪)ታምነው በንጉሡ ከቀራጩ መደብ ከሐጥያት ገበታ ከጥብርያዶስ ባሕር ከጠራቸው ጌታ ስሙን ተሸክመው ቃሉን መሰከሩ በመንፈስቅዱስ ኃይል ድንቅን እየሠሩ አዝ= = = = = የነገስታቱን ቃል ዛቻውን ሳይፈሩ የመንግስቱን ወንጌል ለዓለም አስተማሩ ይሻለናል አሉ ማድላት ለእግዚአብሔር ለሰው ከመታዘዝ ዘላለም ለማይኖር አዝ= = = = = ቆዳቸው ተገፎ በሰይፍ ተሰየፉ ስለጌታ ፍቅር በመከራ አለፉ የድንጋዩን ናዳ የእሣቱን ነበልባል የጀርባን ግርፋት በእምነት ታግሰዋል አዝ= = = = = ስደት ነው መከራ ረሀብ ነው ወይስ ጥም ከክርስቶስ ወንጌል ከእውነት የሚያስቆም በእርሱ ስላመኑ በጽድቅ ተጋደሉ ደግሞም በእርሱ በላይ እንዳለ በቃሉ አዝ= = = = = በዙርያችን ከበው ካሉ እንደ ደመና እነርሱን እያሰብን በእምነት እንፅና በእውነት እንደኖሩ መሥለው ክርስቶስን እኛም በኑሮችን እንምሰል እነርሱን ሊቀ መዘምራን ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ "..ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።" ሐዋ፫፥፮