የገሀድ ፆም ሲፆም ሰኞ ቀኑን ሙሉ እስከ ጥምቀት ቀን ነው ወይስ ሰዓት ገደብ አለው ? ውሃስ መጠጣት ይቻላል ወይ? አመሰግናለው።
Jan 18, 2021የከተራ ዕለት ሰኞ ጾም ነው አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ስለ ገሃድ ጾም እየደወላችሁም እየጻፋችሁም በጠየቃችሁኝ መሠረት ከመጽሐፍ ያነበብኩትን እንሆኝ። እርሶም ታዲያ ለሌሎች ጽሑፉን ያጋሯቸው። ጾመ ገሃድ/ጋድ ቤተ ክርስቲያናችን ከሏት ሰባቱ አጽዋማት መካከል አንዱ “ጾመ ገሃድ” ነው። የገሃድ ጾም የሚጾመው በጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ባለማወቅ የልደትን ዋዜማም “ገሃድ” ብለው ይጾማሉ። ነገር ግን የልደት (ገና) ዋዜማ መጀመሪያውኑ በጾመ ነቢያት ውስጥ ያለ በመሆኑ ገሃድ የለውም። በተለምዶ ግን ጾመ ነቢያትን ሳይጾሙ ቆይተው ዋዜማዋን ብቻ የሚጾሙ አሉ። ጾመ ገሃድ ግን የጥምቀት ዋዜማ ብቻ መሆኑን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያዛል። ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ በሚውሉበት ጊዜ ቀድመው ያሉት ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ። በዚህም ምክንያት ለውጡ ጥምቀት የሚውልባቸው የጾም ቀናት (ረቡዕና ዐርብ) የፍስክ ቀን ሆነው ይከበራሉና። ምክንያቱ ጥምቀት በዓልላችን እንደ ልደቱ፣ እንደ ፋሲካው በታላቅ ቤተ ክርስቲያናዊ ሥርዓት የምናከብረው ታላቁ በዓላችን በመሆኑ ነው። ገሃድ የረቡዕና ዐርብ ለውጥ ነው ካልን እንደ ዘንድሮ በፍስክ ቀንስ ቢውል እንዴት ይሆናል ብንል? ጥምቀተ በዓሉ በሌላም ቀን ለምሳሌ የ2012 ጥምቀት ሰኞ ቀን ውሎ ስለነበር ዕለተ ሰንበትን ጾመናል ዘንድሮ ደግሞ ማክሰኞ ስለዋለ የጥምቀት ዋዜማ ሰኞ ገሃድ ሆኖ ይጾማል። ምክንያቱም ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ገሃድ ስለሆነ እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ስለሚጾም ነው። ነገር ግን “ገሃድ” አንድ ስለሆነ (ስንክሳር የጥር ዐሥሩ መጽሐፈ ስንክሳር እንዲህ ይላል “ሰላም ለዕለት ዋሕድ ዘስሙ ገሃድ” ምንጭ፦✝ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርሐ ጥር ✝“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” መጽሐፍ፤ ገጽ 130። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ታላቁ ያዘጋጁት ለመልዕክት 📩 @TikvahOrthodoxbot ለመቀላቀል ...👇 ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦ ✦✺ @tikvahorthodox ✺✦
Jan 18, 2021