Guys ቶ meskel be Orthodox haymanot west mn tergum endalw kawkachu ngrune😊
Jan 16, 2021@felegeTibebat if u want to look up the rest.
Jan 16, 2021Guys ቶ meskel be Orthodox haymanot west mn tergum endalw kawkachu ngrune😊
Jan 16, 2021@felegeTibebat if u want to look up the rest.
Jan 16, 2021የ "ቶ" ቅርጽ መስቀል የዚህን መስቀል ትርጉም እጅግ በጣም ብዙ ፀሐፍያንና የከርሰ ምድር ታሪክ መዝባሪዎች ምሁራን ቢመራመሩትም እስከ አሁን ድረስ ግራ ቢገባቸው "The lost image of cross"(እስካሁን የጠፋው ታላቅ ሀይል ያለው የመስቀል ምልክት) በሚል ጽሁፍ አበርክተዋል። እጅግ ምሥጢራዊነቱ የሚነገርለትና የተጻፈለት ይህ በ "ቶ" ፊደል ስለተቀረጸው መስቀል ካነበብኩት በጥቂቱ ላጋራችሁ። "ቶ" ሰባተኛው ፊደለ ነች። ሰባት ቁጥር ትልቅ ትርጉም ያላት ፍጹምነትን የምትገልጽ ነች። ሰባተኛዋ ሰማይ ዙፋን የጌታ እንደሆነ፣ሰባተኛው ቀን ሰንበት እንደሆነ፣..7 ቁጥር ብዙ ምስጢር አላት። "ቶ" 7ኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍጹምነትን የምታመለክት ነች። ክርስቶስን የምትወክል ነች። ፍጹምነቱን። "ቶ" ተለይታ ፍጹምነቱን ትገልጻለች የተባለበት ምክንያት እንደ ቤ/ክ አስተምህሮ እያንዳንዱ ፊደላት (ሀ፣ለ፣ሐ፣መ፣ሠ፣ረ፣ሰ፣ሸ፣ቀ፣በ፣ተ፣ቸ...) የየራሳቸው የሆነ ትርጉም አላቸው። "ተ" ፊደል ጋር ስንደርስ ያለው ትርጉም ከክርስቶስ ኢየሱስ ፍጹም ሰውነትና አምላክነት እንዲሁም ስቅለት የሚገልጽ ይሆናል። የዚችው የ"ተ" ቤት ዘር ሰባተኛ ፊደል "ቶ" ደግሞ ይበልጥ ፍጹምነቱን ያሳያልና ነው። ትልቁ ከዚ በላይ ያለው ምሥጢር አባቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜን ሲተነትኑ በሰማይ መላዕክት ዘንድ ያኔ ውግያ ሲሆን ሚካኤልና መላዕክት ሁለቴ ተሸንፈዋል። በሦስተኛው ሊዋጉት ሲሄዱ እግዚአብሔር አምላክ ይህን ቀስተ ደመና ቀርጾ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርጽ የ "ቶ" ቅርጽ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርጾላቸዋል። "ኤል" የሚለውንም ምስጢራዊ ኃያል ስም አትሞባቸዋል። ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ኃይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም። ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት። ይህ ላቲኖች "መያዣ ያለው መስቀል" በማለት የሚጠሩት የመስቀል አይነት በጥንታዊ ግብጽ ሄሮግላፊክ ጽሑፎች ላይ እጅግ የተለመደ ነው። የታሪክ መዛግብቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ቀደምት ግብጻውያን ክርስቲያኖች የኦርቶዶክስ ክርስትናን በተቀበሉ ወቅት ይህንን የ "ቶ" ምስል ወደ ክርስትናው አምጥተው አጥምቀውታል። በአሁኑም ሰአት የኮፕቶች መስቀል ወይም በላቲን "ክሩክስ አንሳታ"(crux ansata) በመባል ይታወቃል። በኢየሩሳሌም ዩኒቨርሲቲ የከርሰ ምድር ጥናት ክፍል ስር እና በዶ/ር ኤሊያት ማዘር መሪነት በተደረገ ቁፋሮ ወቅት፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመጽሐፈ ነገስት ካልዕ ላይ የተጠቀሰው የአካዝ ልጅ ንጉስ ሕዝቅያስን መንግስት ምስል የያዘ ሸክላ የተገኘ ሲሆን በላዩ ላይም "ቶ" ተቀርጾበት ተገኝቷል። ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ አውሳቢዮስም የጻፈውና በግዕዝ ቋንቋ ሃገራችን የሚገኘው ትርጓሜ እንደሚያሳየው ከሆነ ትምህርትን፣ተግሳጽን፣ተዓምርን ለመለያየት ብዙ ምልክት ተጠቅመዋል። ከነዛም አንዱ "ቶ" መሰሉ ፊደል ነው። ይህ የ "ቶ" ቅርጽ መስቀል አገልግሎት የጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት 300 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብጻውያን ቶርኔተር(የፑንት ምድር) ብለው በሚጠሯት ሃገር ነው። ግብጻውያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶርኔተር(የአሁኗ ሃገራችን ኢትዮጵያ) ሰዎችና አማልክቶች ነው። በ670 ዓ.ዓ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው ንጉስ ቲርሀቅ ኢየሩሳሌም የአሶር ንጉስ በሆነው በሰናክሬም ስትወረር ለኢየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ሀያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የ "ቶ" ምልክት እንደተቀረጸና ንጉሱም በ "ቶ" ቅርጽ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ተገኝተዋል። የ "ቶ" ምልክት መስቀል የተፈጠረው በቅርብ ጊዜ ነው ለሚሉ ሰዎች "ቶ" የተፈጠረው ዓለም ሰፈጠር ነው ቢባል እውነት እንጂ ውሸት አይሆንም። ለዚህ ማስረጃው ደግሞ የሰው ልጅ ራሱ የተፈጠረው ስናስተውለው በ "ቶ" ቀመር መሆኑ ነው። ይህ ምልክት በግብጽ የሚገኙ የዋሻ ስዕሎች ላይ የሕይወት ገጸ ባህሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ ምልክት አገልግሎት የጀመረው ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብጽ ላይ እንዴት ተገኘ?ብሎ ለሚጠይቅ ግብጽ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ነገስታት ተጠቃሽ ናቸው። ሜምኖን የተባለው ኢትዮጵያዊ የግብጽ ንጉስ ከ1320 አ.አ(አመተ አለም)እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም(አመተ ምህረት)የቆመ ሀውልት እንደነበረና ሀውልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሐይ ሲያርፍበት የክራር ድምጽ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል። ክራር ደግሞ የኢትዮጵያ የባህላዊ መሳሪያ መሆኑ አጀብ ያስብላል። በሳባውያን(ኢትዮጵያውያን) የዋሻ ላይ ስዕሎችና ማህተሞች ላይ "ቶ" ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ አስቻለው ከበደ የተባለ ፀሐፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ በሚል መጽሐፉ አስፍሮታል። ሳባውያን(ኢትዮጵያውያን) ሰውን ለመሳል "ቶ"ን መጠቀማቸው ያጋጣሚ ይመስላችኋል?በትምህርት ቤት ለምሳሌም ለምኑም ሰው ሲሳል "ቶ" እንዲ እንደሚሳል አስተውላችኋል?በሮማውያን አፈታሪክ ላይ የሕይወት ምልክት ተደርጎ የተወሰደው የተጋደመው የ "ለ" ፊደል ሲሆን በግራና በቀኝ ሁለት ጭረቶች አሉት። ይህ ምልክት ለሮማውያን ከአማልክቱ የተሰጠ መስሎ ቢታያቸውም እውነቱ ግን በአንድ ባልታወቀች የአፍሮዳይት ኦራክል የተፈጠረ እንጂ የህይወት ምልክት ላለመሆኑ ከሰው ጋር አብሮ የተፈጠረው የ "ቶ" ምልክት አስረጂነቱ ብዙ ነው። ለምሳሌ እንኳን ብንወስድ ጠቢቡ ሰሎሞን ታላቁን ቤተመቅስደ ከመስራቱ አስቀድሞ በሚሰራበት ቦታ ላይ አሰድ እሳት የሚሰኝ ኮከብና ጸሀይ በ45 ዲግሪ ትይዩ ወተውጥ ነበር። በዚህም የተነሣ እስራኤል የአንበሳ ከተማ ተብላ ትንቢት ተነግሮላታል። አንበሳ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ መለያ ምልክት እንደሆነ ልብ ይበሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ወቅት ይህ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ ከጸሐይ ጋር ትይዩ ሆኖ በመውጣት የጌታችንን ንጉስነት አብስሯል።ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅትም ጸሐይን ጨምሮ የተለያዩ ኮከቦች የመስቀል ቅርጽ ሰርተው። በኢየሩሳሌም አናት ላይ ታይተዋል። በተጨማሪ ስለ "ቶ" ምልክት የኢትዮጵያን ምሥጢራዊ ታሪክ በማጥናት አለም አቀፍ እውቅና የተሰጣቸው አባ ተስፋሥላሴ ሞገስ ይህን ጽፈዋል፦ "...ክርስቶስን የሚወክለው "ቶ" ፊደል የተደረገበት (በመጽሐፋቸው ላይ በኢትዮጵያ ካርታ መሀል የ "ቶ" አርማ ይገኛል) ከዓለም ሕዝብ በፊት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ኦሪትን ከሐዲስ ጋር አዋህዳና አስማምታ የምታምንና የምታሳምን ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን የሚያመለከት ነው..." /ምንጭ፦"ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሳም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" የተሰኘው የአባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ መጽሐፍ/ "ቶ" እስካሁን ከተመለከትነው ትርጉም ባሻገር ሌላም ትርጉም አለው። "ቶ" አቶ ወይንም እኔ ማለት ነው። አ፣ኦ ያሉት ቃላት ከጉሮሮ ተነስተው በአንደበት የሚሰራጩ አናባቢዎች ናቸው በዚህ መሰረት አ አናባቢ ሲሆን ተነባቢው ቶ ነው ማለት ነው። ከዚህ በመነሳት ቶ ከስም ቀድሞ የሚገባ ባለቤትን አመልካች ነው። ይህ ምልክት ከሱባ ቋንቋ ጋር ተዛምዶ እንዳለው መራሪስ አማን በላይ በመጽሐፋቸው ጽፈዋል።
Jan 16, 2021Menem tergum yelewem. Ke EOTC ga mnm aygenagnewem. It related with Jewish religion and old Egyptian gods or Pharaoh
Jan 16, 2021kmr agelaletsesh temechlognal
Jan 16, 2021Ye ቶ meskel anget laymareg ayfekedm bebetekrstian
Jan 16, 2021"ቶ" የግዕዝ ቋንቋ ህያዊ ነው:: የተፈጠረውም ለምስጋና ነው:: አባታችን አዳም: እናታችን ሄዋን ፈጣሪያቸውን ያመሰገኑበት ህያዊ ቋንቋ ነው:: በዚህ መሰረት የፊደላቱ ጠልሰም ትርጉሙም ምልክቱም ምድራዊ ብቻ ሳይሆን ሰማያዊም ጭምር ነው:: ለዛሬ ለምናየው የ "ቶ "ን ትርጉም እና ጠልሰማዊ ሁናቴሁን ይሆናል፡፡ ቶ ጠልሰም ትርጉም: ክርስቶስ ተነስቷል በአባቱም ቀኝ ተቀምጧል:: አዳም ዳግም ወደ ክብሩ ተመልሷል:: በስሙ ለሚያምኑት ለተጠሩት ልጅነትን ከሃይል ጋር ሰጣቸው:: የሰማይናንና የምድርንም መክፈቻ ቁልፍ ሰጣቸው:: በማለት አባቶች ያመሰጥሩታል:: ስለ #ቶ ጠልሰም[ ምሳሌ፣ አርማና ምልክት] የኢትዮጵያን ምስጢራዊ ታሪክ በማጥናት አለምአቀፍ እውቅና የተሰጣቸው አባ ተስፋሥላሴ ሞገስ ይህን ፅፈዋል: ",,,,, ክርስቶስን የሚወክለው "ቶ" ፊደል የተደረገበት ( በመፅሀፋቸው ላይ በኢትዮጵያ ካርታ መሀል ላይ የ "ቶ"አርማ ይገኛል) ከዓለም ሕዝብ በፊት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ኦሪትን ከሐዲስ ጋር አዋህዳና አስማምታ የምታምንና የምታሳምን ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን የሚያመለክት ነው, ,,," እንዲሁም በሚስጥር የተሞላች መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይሁን እና በገባወት ቃል መሰረት ይህን የ ቶ ሚስጥራዊ ፊደል ትርጉሙን ሳፈላልግ ሰዉ ስጠይቅ እንዲሁም መርጃ ሳሰባስብ እንዲህ የሚል አገኘሁ "ቶ"( before christ 3000Bc ) known as" ANKH" is an ancient Egyptian hierogly symbol that was most commonly used in writing and in art to represent z word life But z origins of z symbol are not known.ይላል ይህ ankh ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመተ አለም ግብፃዊያን የሂወት ምልክት ነዉ ብለው ሲጠቀሙበት እንደነበር እና የዚህ ምልክት ባለቤቱ ግን ማን እንደሆን አይታወቅም ይላል፡፡ ከዚህ ላይ አስተዉሉ ይህን መነሻ ሀሳብ ይዠ መረጃ ፈለጋ መኳተኔን ቀጠልኩ አንድ ነገር አስታወስኩ በአንድ ገዳም ዉስጥ ያየሁትን እንደገና ማስተዋል ጀመርኩ ነገሩ እንዲህ ነበር በእድሜዉ ዘመናትን ያስቆጠር ጥንታዊ ገደም ውስጥ ተቀምጫለሁ፡፡የተጓዝኩት ከባህር ዳር ወደ እስተ ሰሜን አቅጣጫ ነበር መንገዱ እጅጉን አድክሞኛል ይህ ጥንታዊ ገዳም ግርማው የሚያሰፈራ እንዲሁም በዉሀ የተከበበ እጅጉን የሚማርክ የእፅዋት ሽታ ያለበት ነዉ፡፡ ወቅቱ የጥቅምት ወር በመሆኑ የመሬቱ እርጥበት እንዳለ ነዉ፡፡ ከገዳሙ ስደርስ ፀሎቴን አድርሸ የተወሰነ እራቅ በማለት ከዛፉ ስር ተገድፌ ቁጭ ብየ የገዳሙን የተፈጥሮ አቀማመጥ በመገርም አየዋለሁ፡፡ በአካባቢየ ምንም ሰዉ የለም ግን ከቤተመቅደሱ ያሬዳዊ ዜማ እሰማለሁ ልዩ የሆነ እጣንም ከቤተክርስቲያኑ ጣራ ስር እንደ ምንጭ ዉሀ ይወጣል፡፡ ከመቀመጫቸ ተነስቸ ጫማየንም ሳልጫማ ወደ ቤተክርስቲያኑ ተጠጋሁ ስሰማዉ የነበር ዜማ ዝም አለ በመገርም ወደ በሩ ተጠጋሁ ወደ 3 ሜትር የሚረዝመዉ የእንጨት በር ተቆልፏል፡፡ በጣም ደነገጥኩ ላብ በራሴ ላይ ሲወርድ ታወቀኝ የፍረሀት ካባ ተጫነኝ፡፡ ማንን ነበር የሰማሁት? የምን ድምፅ ነበር የሰማሁት?? ካለሁበት ፈዝዠ ቀረሁ እራሴን አርጋጋሁ እና በፊት ተቀምጨባት ከነበር የግራር እንጨት ከዛፉ ስር ተቀመጥኩ፡፡ ከ 20 ደቂቃ በኀላ እንድ አዛዉት መነኩሴ ከ ተዘጋዉ ቤተክርስቲያን ሲወጡ ተመለከት፡፡ የፈጣሪ ያለህ! የት ነበሩ አልኩ ለራሴ፡፡ አዛወንቱ የወይራ መቋሚያቸዉን በግራ እጃቸው ተገድፈዉ ቀኝ እጃቸውን ወደ ውስጠኛው የግራ ደረታቸዉ ሲያስገቡ አየሁ የሆነ ነገር ሊያወጡ ይጣጣራሉ፡፡ እንዳላዮኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከ አንገታቸው በጥቁርገመድ የታሰር ወደ 30 ሴሜ የሚረዝም ያረጀ እና የማረተ የ "ቶ" ቅርፅ ያለው ቁልፍ አውጡ በሩንም ቆለፉ፡፡ አሁን ላይ ሳስታዉለዉ እዉነትም ነገር አለዉ አልኩ፡፡ ያኔ መረጃየን ማሰባሰብ ጀመርኩ፡፡ በሩን ቆልፈው ወደ ባእታቸዉ ሲመለሱ እነዴት ዋሉ አባ አልኩዋቸው፡፡ ዞር በለዉ በአንገታቸው ሰለምታን ሰጠወኝ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ አባ አልኳቸዉ በደጋሚ ዙረዉ ተመለከቱኝ እና ምን ፈልገህ ነዉ ገብር ስላሴ አሉኝ ፡፡ የፈጣሪ ያለህ ስሜን የት አወቁት አልኩና በልቤ እሱን ከአንገትወት ያሰሩት የ ቶ ምልክት ብዙ ቦታ ላይ አይቸዋለሁ መፃህፍት ላይም ተፅፉዋል ዛሬም ከስዉ አንገት አየሁት ግን ሚስጥሩ ምንድን ነው አልኩዋቸው ? ትንሽ እንደማቅማማት አሉና የአባቶችን ጥበብ ፈለጋህ ይበል ነዉ ገብር ስላሴ ና ተከተለኝ አሉኝ እኔም ከኀላቸዉ ተከተልኳቸዉ....... ይ ቀ ጥ ላ ል፡፡ ጥበብን ፍ ለጋ ......@ felegetibebat
Jan 16, 2021Bzu neger new gn tikikilegna mereja ke betekristian bitisemi arif new
Jan 16, 2021En ቶ meskeln mawekewu dortogada mestafe layi nw 🤷♂
Jan 17, 2021Nothing to do with our church
Jan 16, 2021I am not orthodox but dertogada lay ena sewoch lay ayichalew
Jan 16, 2021Muslim negn gn endemimeslegn tedros nw trgumu gedam ale mibalew meri
Jan 16, 2021Ytefekede aydelem... mikniyatum fetari ymotew to meskel lay sayhon ytemesakele inchet lay nw... To meskel ynigus milikit enji ye kristos aydelem...✌️
Jan 16, 2021