#business Internet access kalegn endet nw bet hugne ewnetegna genzeb mesrat mchlew
Jan 10, 2021Gn english language or France perfect bathon yemeredat aqmu linorh ygebal then follow me👇 #ኦንላይን_ስራዎች_ለምትፈልጉ አንዳንዶቻችሁ ኮምፒውተርና ኢንተርኔት በመጠቀም ቤታችን ቁጭ ብለን ኦንላይን የምንሰራው ስራ ካለ ብትጠቁመን ብላችሁ ትጠይቁኛላችሁ፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ዘመን ሁሉም ስራዎች ኦንላይን እየሆኑ መጥቷል፡፡ ሰዎች በኮምፒውተርና ኢንተርኔት አማካኝነት ቤታቸው ቁጭ ብለው የተለያዩ ስራዎች ለተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች በመስራት ከፍተኛ ገቢ ያገኛሉ፡፡ ኦንላይን ስራዎች በጣም እየተለመዱ መጥቷል፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች ብዙም ማሰላሰል የማይጠይቁ ስራዎች ለምሳሌ፡- ዳታ መመዝገብ፡ መፅሀፎችን ፊደል ማረም፤ድምፅን ወደ ፁሁፍ መገልበጥ፤ወዘተ ስራዎች በስፋት ኦንላይን ያሰራሉ፡፡ ኦንላይን ስራዎችን በመስራት ጥሩ ገቢ ማግኘት እያሰባችሁ ያላችሁ ሰዎች ካላችሁ ኦንላይን ልትሰሯቸው የሚችሉ 3 ስራዎች ልጠቁማችሁ፡፡ 1ኛ፡- Copy Editor ጥሩ የእንግሊዘኛ ቋንቃቋ እውቀት ካላችሁ ይህ ስራ በጣም ጥሩ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ብዙ ኦንላይን ስራዎች አሉ፡፡ በዚህ ዘርፍ ከናንተ የሚጠበቀው ስራ የተለያዩ ፁሁፎች ይሰጣችኋል ። ከዚያ ያንን ፁሁፍ ፊደል ማረም ነው፡፡ፊደል ማረም ሲባል ፁሁፉ ላይ ቃላት የተገደፉ ካሉ ማስተካከልና ማረም የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ዌብሳይቶች፤መፅሀፍት፤መፅሔቶች እና የመሳሰሉትን እንድታርሙ ትጠየቃላችሁ፡፡ ጥሩ ስራ ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት ኦንላይን ስራ ከፈለጋችሁ "copy editor online jobs" ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ 2ኛ፤- Transcriber ይህ ኦንላይን ስራ ሪከርድ የተደረገ ድምፅ ይሰጣችኋል፡፡ድምፁን እያዳመጣችሁ ወደ ፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ለምሳሌ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ንግግር ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ በፁሁፍ መተርጎም ነው፡፡ በተለይ እንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ ችሎታ ያላችሁ ይህ ጥሩ ስራ ይመስለኛል። የሚሰጣችሁ ድምፅ ንግግር፤ስብሰባ ላይ የተደረገ ንግግር፤ቪዲዮ ኮንፈረንስ ሊሆን ይችላል፤ትምህርቶች ሊሆን ይችላል፡፡ወዘተ Online Transcriber Jobs ብላችሁ ጎግል ብታደርጉ ብዙ ስራዎችን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ 3ኛ፡- Data Entry ይህ ኦንላይን ስራ የተለያዩ መልክ ያልያዙ ዳታዎችን መመዝገብ ነው፡፡ ለምሳሌ የትምህርት ቤቶች ወይም የሆስፒታል ትልልቅ ዳታዎችን ወደ Excel ማስገባት ወይም መመዝገብ ማለት ሊሆን ይችላል።፡ በተለይ ቁጭ ብሎ የመስራት ትዕግስት ያላችሁ ሰዎች ይህ ስራ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ኦንላይን ስራዎች ለመስራት ኢንተርኔትና ኮምፒውተር ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡ ከላይ ከገለፅኳቻው ስራዎች ውጪ ሌሎች ብዙ ኦንላይን ስራዎችን ብትፈልጉ ታገኛላችሁ፡፡ሞክሩ፡፡ 🍡የዩቲዩብ ቻነሌን እግረመንገዳችሁን ሰብስክራይብ አድርጉ 👇 https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
Jan 10, 2021