#religion Nisha gebtachu mtaku and bezi ngr lay ewket yalachu. Nsha megbat felge nbr ena yeserahutn hatyat specif detail menager alebign like i used to masturbaate or sext mnamn bye or generalise arge new menager yalebgn ? I need ya'll's help By: Anonymous Ask Anything Ethiopia
Jan 09, 2021ንስሃ ላይ ሽፍንፍን ሚባል ነገር አይሰራም ። ሁሉንም ነገር ግልጥልጥ አርገን መንገር አለብን ። ንስሀ ስንገባ ሀጥያትን ለካህን መንገር ያስፈለገበት ምክንያት ራሱ እኮ በሰራነው ሀጥያት እንድናፍር ነው ። መቼስ እኛ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ነው ምንፈራው ሀጥያትን እግዚአብሔር ፊት ምንም ሳይመስለን እየሰራን ሰው ፊት ሲሆን ግን እንኳን እያዩን ሀጥያቱን መስራት ይቅርና ለመናገር እናፍራለን። ለዚ ነው ብዙ ሰዎች ሀጥያታቸውን መናገር አፍረው "ሀጥያት የተባለውን ነጠር ሁሉ ሰርቻለው' የሚሉት ። እውነተኛ ንስሀ ላይ ግን እንደዚ አይሰራም ሀጥያታችንን በዚ ቀን እንደዚ እንደዚ አድርጌያለው ብለን ግልጥልጥ አርገን መናገር አለብን ። ይሄም የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ነው። " እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።" (የያዕቆብ መልእክት 5:16)
Jan 09, 2021