Hi Guyz, If u answer this question and clarify it to me, I will thank you forever! እኔ ክርስትያን ነኝ፤ በእግዚአብሔር አምናለሁ። ኦርቶዶክስ is ከperfect እና perfect በላይ። ግን አንድ ነገር ሁሌም ናላዬን ያዞረዋል፤ Predestination. እና ይህ predestination የተባለ ነገር አንድ ሁኔታ ወይም ተግባር ከመደረጉ በፊት predestined ተደርጓል(አስቀድሞ እንዲሆን ታቅዷል)። እና መንገድ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን በማመኔና ኢየሱስን በተግባር እንዳውቅ የረዳችኝ ቅድስት ቤተክርስትያንን በመከተሌ በጎ ተግባራትን በማድረጌም ፀድቄ ገነት እንደምገባ አምናለሁ። ሌሎቹም ሀይማኖቶችም እንደዛ ይሰብካሉ፤ እምነታቸው ገነት እንደሚያስገባ። እናም ያለን አንድ አምላክ ነውና ይህን አምላክ በትክክል የገለፀ እምነት አይደል ትክክለኛ መንገድ? So let's say Orthodox is the only way and 1 religion that God has created for us to let us join his Paradise. በPredestination ህግ መሰረት፣ አንድ ልጅ ገና ሳይወለድ ከምን አይነት እምነት ተከታይ ቤተሰብ እንደሚወለድ አስቀድሞ ተወስኖለታል!! ከሙስሊም ከተወለደ ሙስሊም ይሆናል። ከላይ ባስቀመጥኩት Premise መሰረት ይህ ሰው አይፀድቅም ማለት ነው፤ ምክንያቱም ኦርቶዶክስ ስላልሆነ(በpremise መሰረት ስላልኩ አስተውሉ)። ከጴንጤ የተወለደ ጴንጤ ይሆናል ግን አይፀድቅም። ከቡድሂስት የተወለደ ቡድሂስት ይሆናል ግን አይፀድቅም ማለት ነው... እና የኔ ጥያቄ እግዚአብሔር የሰራው ሀይማኖት አንድ ከሆነ፣ የሚመለክበትም ስርዓት አንድ ከሆነ፤ ታድያ ለምንድነው predestined ሆነው የተወለዱ ሰዎች አይፀድቁም ማለት የምንችለው? Predestined የሆነ ሰው ለምን በPredestination ብቻ መፅደቁ ወይም አለመፅደቁ ይወሰናል? ጥያቄዬ ካልገባችሁ ኮመንት ላይ ጠይቁኝ።
Jan 08, 2021Predestination እና foreknowledge ልዩነት አላቸው እግዚአብሔር ሁሉን ቀድሞ ያውቃል ምክንያቱም ከኛ ጊዜ መስፈሪያ በላይ ስለሆነ ነው ። ነገር ግን እሱ ያን ነገር እንዲፈጠር አደረገው ማለት አይደለም ። ለምሳሌ አንድ ሰው ቀድሞ ይየውን ፊልም ቤት ወስዶ ቢያሳያቸው እና ገና ሳይጨርሱት እንዲ እንዲ ይሆናል ብሎ ስለፊልሙ ቢነግራቸው እና ያለው ቢሆን ያ የሆነው እሱ ስላለው ሳይሆን እሱ ቀድሞ ስላወቀው ነው። እግዚአብሔር ሁሉን አስቀድሞ ያውቃል ይህም አምላክ ስለሆነ ነው ግን እሱ እንዲሆን አደረገው ማለት አይደለም። free will (ነጻ ፍቃድ )እና ህግ የተሰጠበት ዋነኛ ምክንያት ይሄ ነው ። አስቀድሞ የሚወስን ቢሆን ኖሮ ለምን ህግ እና መንፈሳዊ ትምህርት አስፈለገ? ለምሳሌ አንድ ሰው ቤት ውስጥ ቆልፈነበት አትውጣ ብንለው ልክ አይደለም ። ግን ክፍት በር አድረግን አትውጣ ብንለው ነጻነት (ነጻ ፈቃድ)እንዳለው ርግጥ ነው ህግም የሚያስፈልገው ነጻነት ስላለን ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉን ቀድሞ ያውቃል እንጂ ሁሉን ቀድሞ አልወሰነም ። ለመጽደቅ ደግሞ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት እምነት እና ምግባር እና የእግዚአብሔር ቸርነት ያስፈልጋል ። እምነት ተዋሕዶ ምግባር ባዶ ከሆነ ጽድቅ የለም ።
Jan 09, 2021