የ እንጀራ ታሪክ ከየት ነው ሚጀምረው 🙄
Jan 04, 2021ታሪኩ ሰፊ ቢሆንም በአጭሩ የእንጀራ ታሪክ እንዲህ ነው፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት 1400አመት አካባቢ ዘንዶ/ኔፍሊም በአለም ሁሉ ላይ ይነግሱና ይመለኩ ነበር(በተለያዩ ሃገራት የጥንት ሃውልቶችና ስእሎች ላይ እንደምናየው)፣ ታዲያ እግዚአብሔር አምላክ ህዝቡን ነጻ ሊያወጣ ወዶ አንድ አንጋቦስ የሚባል ኢትይጵያዊ ያስነሳና ሃይል ሰጥቶት ዘንዶውን ራስ ራሱን ቀጥቅጦ ኢንዲገድል ያደርገዋል ህዝቡም 'አሁን ምን ልንበላ ነው የሚያበላን ንጉሳችን እና አምላካችን ሞቷል' አሉ ታዲያ ፈጣሪያችን ይህን አይቶ የሞተው ዘንዶ ወዲያው እንዲቃጠል ከዛም እያዩት እንዲበሰብስ ቀጥሎም በሚገርም ሁኔታ ከብስባሹ ላይ የምመግባችሁ እኔ ነኝ ሲል ጤፍ አብቅሎ ሰጣቸው። ለዛ ነው መዝሙረኛው ዳዊት በመዝሙር 73:- 14፤’’አንተም፡የዘንዶውን፡ራሶች፡ቀጠቀጥኽ፤ለኢትዮጵያ፡ሰዎችም፡ምግባቸውን፡ሰጠኻቸው።’’ ያለው። ብዙዎች ታሪኩን ሊያጠፉ ቢሞክሩም የኢትዮጵያ ኦርትሆዶክስ ቤተክርስቲያን ይህን እውነት ታስተምራለች፣ ቦታው መንዝህ/መንዝ እመጓዋለ ቆላ የሚባለው አካባቢ ነው ይባላል፣ የዘንዶው መሰዊያ የነበረ ቦታም እዛው አለ፣
Jan 05, 2021