ስለ ጌታችን መድኃኒቶችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ የተነገሩ ትንቢቶችን ከነጥቅሳቸው ብትነግሩኝ
Jan 03, 20211. “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” — ኢሳይያስ 7፥14 2. “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” — ዘፍጥረት 3፥15 3 “እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።” — ሉቃስ 1፥31 4. “ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” — ማቴዎስ 1፥21 5. “እርሱም እስራኤልን ከኃጢአቱ ሁሉ ያድነዋል።” — መዝሙር 130፥8 6. “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” — ኢሳይያስ 9፥6 7. “በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።” — ኢሳይያስ 53፥2 8. “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።” — ሉቃስ 2፥11 በጣም ብዙ አለ search for it ለኛ ሲል ሰው ለሆነልን ጌታ የማናሳፍር ታማኝ በጎ ባሪያ እና ልጅ ምንሆንበት ፀጋ ይብዛልን
Jan 04, 2021