#for_Orthodox (ራእ 22 ) ------------ "8 ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። 9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።" የክብር እና የአምልኮ ስግደት እንዳለ ሰምቻለሁ ነገር ግን መልአክት የልባችንን አያውቅም የክብር ይሁን የአምልኮ እንደሰገደ አያውቅም ስለዚህ ስግደት ቢገባው ሲሰግድለት ስግደቱን ይቀበል ነበር የልባችንን ይረዳል ቢባል ራሱ ለምን የክብር ስገድልኝ አላለም ለምን #እንዳታደርገው_ተጠንቀቅ አለው? ምክንያታዊ የሆነ መልስ ስጡኝ ?
Jan 01, 2021✝✝ዮሐንስ ራዕይ ➕19 ➕ 10✝✝ ✝✝በኦርቶዶክስ አስተምህሮ ✝✝ ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የዮሐንስ ራእይ 19 : 10 ✍✍መናፍቃን ይችን ጥቅስ በመጥቀስ ለመላዕክት መስገድ ተገቢ አይደለም ይላሉ። ✍✍ይህም ስህተት መሆኑን እንመለከታለን ቃሉም ለምን እንደተነገረ እና መላዕኩ ለኔ አትስገድ ያለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን ✝✝እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን✝✝ ✍✍የመልአኩ አባባል እንደሚናፍቃኑ አባባል አይደለም እና እንዴት ነው ብለን ከጠይቅን ኑ ተከተሉኝ እንየው ✍✍ታድያ ዮሐንስ ለመላዕክት መስገድ ከሀይማኖት ውጪ ሆኖ ባለማወቅ የሰገደለት ሆኖ አይደለም። ይህንንማ እንዳንል የሰጋጁ የዮሐንስ ማንነት ያግደናል ።ዮሐንስ ድንግላዊ እና የጌታ ሐዋርያ ከመሆኑም ሌላ ጌታ የሚወደው በመንፈስቅዱስ የተቃኘ ወንጌልን መልዕክቶች የጻፈ እንዲሁም የአለምን ፍጻሜ በራዕይ ያየ ነው። ✍✍ይህን ያህል የጌታ ባለሟል የሆነ ቅዱስ ሰው ስለትንሽዋ ነገር ለመላዕክት መስገድ ተገቢ አለመሆን አጥቶት ሳይረዳ ቀርቶ በስህተት ሰገደ ማለት የጻፋቸው ወንጌሎችም መልእክታትም ስሕተት አላቸው ማለት ነው።ይህ ማለት ሰው እንደ እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት አይደለም ✍✍እሱ በፍጹም እምነት ውስጥ ሳይሆን እሱ ማን መመለክ እንዳለበት ሳያውቅ ለእኛ ማሳወቅ አይችልምና ✍✍ ስለዚህ በስህተት ሰገደ ማለት ከፍተኛ ስህተት ነው።ተ ዮሐንስ ለመልአኩ የአክብሮት ስግደት ያቀረበው ለመላዕክት መስገድ ተገቢ መሆኑን ስለሚያውቅ ነው። ✍✍መልአኩ ደግሞ አትስገድልኝ ማለቱ የዮሐንስን ክብር እና ማዕረግ መግለጹ ነው።ዮሐንስ በክብሩ ከመልአኩ እኩል ሆኖ ነበርና።ስግደት ደግሞ በባህሪው የበላይ እና የበታች መግለጫ ስለሆነ አንተ እኮ በክብር ከእኔ እኩል ነህ ስለዚህ ለእኔ ልተሰግድ አይገባም ቢለውም ዮሐንስ ግን ከመስገድ ወደኋላ አላለም ትሁት ነውና። ✍✍ይህንን ለማረጋገጥ ከፈለግን ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ። የዮሐንስ ራእይ 22 : 8-9 ✅እንግዲህ ዮሐንስ ተሳስቶ ሰገደ ብንል እንኳን ሁለት ጊዜ ይሳሳታል ?የመጀመሪያው አንሶ? እንግዲህ የመልአኩ አባባል የትህትና አባባል መሆኑ ግልጽ ነው። ለግሩፕ @mediam_meder ለቻናል @ymediam_meder ለአስተያየት @mediam_mederbot
Jan 01, 2021