Hey guys... My period simeta betam nw miyamegn ena ras metat ena alchalkum betam ena please ras metatun matefabet menged kale erdugn ebakachu, medhanit dmo yelemdal eyalugn eferalew ena mokerem it doesn't work bcha miyamachu seroch endet nw metaregut?
Dec 21, 2020ጤና ይስጥልኝ! በጣም ብዙዎቻችሁ በወር አበባ ጊዜ ስለሚከሰት ህመም እየጠየቃችሁ ነው። አጠር ያለ ነገር እነግራችኋለሁ። በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ህመም አይነቶች 1.primary dysmenorrhea(ያለ ምክንያት የሚከሰት) 2.Secondary dysmenorrhea( በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት-ለምሳሌ በእጢ ምክንያት ወዘተ) 1.primary dysmenorrhea(ያለ ምክንያት የሚከሰት የወር አበባ ህመም) - ከ60 -90% ወጣት ሴቶች ላይ ይከሰታል -ምክንያቱ- prostaglandin የተባለ ንጥረ ነገር በብዛት መመረት ህክመና- የሐኪም ቅርብ ክትትል የሚያስፈልግ ሲሆን፣ህክምናው ደረጃ በደረጃ ይሰጣል ደረጃ 1 ህክምና- Ibuprofen and Diclofenac የመሳሰሉት ሲሆን በሁለቱ ህመሙ ካለቀነሰ Mefenamic acid መጠቀም ይቻላል መቸ መወሰድ አለባቸው? መጠነኛ ህመም ከሆነ- የወር አበባ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ ለሁለት ቀን ከባድ ህመም ከሆነ- የወር አበባ ከመጀመሩ 1 ወይም 2 ቀን ቀደም ብሎ መጀመር እና የወር አበባ ከጀመረም በኋላ መቀጠል ደረጃ ሁለት ህክምና- ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ወስዳ መሻሻል ከሌለ የወሊድ መከላከያ እንክብል እና ሌሎችን መውሰድ ደረጃ ሶስት ህክምና-ከላይ ደረጃ 1 እና 2 ላይ የተጠቀሱትን አጣምሮ መጠቀም ይመከራል ተጨማሪ ህክምናዎች ነገር ግን የን ያህል ውጤታማ ያልሆኑ አማራጮች - ሙቀት ያለው ነገር ሆድ ለይ ማስቀመጥ እና እንቅስቃሴ ማረግ ከላይ ባሉት ህክምናዎች ለውጥ ከሌለ secondary dysmenorrhea(በምክንያት የሚመጣ የወር አበባ ህመም ሊሆን ስለሚችል እንደገና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል) የsecondary dysmenorrhea ምክንያቶች ምን ሊሆን ይችላል? 1. Anatomic abnormalities(ማህፀን አካባቢ ያሉ የአፈጣጠር ችግሮች) 2.Endometriosis እሚባል ችግር 3. የማህፀን ኢንፌክሽን 4. የማህፀን እጢ(የተለየየ አይነት ሊሆን ይችላል) 5. ጭነቀት እና ሌሎችም ህክምናው- ለህመሙ ምክንያት ሆኖ የተገኘውን ማከም ። ለምሳሌ የማህፀን እጢ ከሆነ በቀዶ ህክምና እንዲወጣ መድረግ። ጤና ይስጥልን! We work for evidence based women health!! Lela merja kefelgesh save yarekut ale felge lekeleshalewu
Dec 22, 2020