ጋይስ የሀይማኖት ጥያቄ መጥቷል በመመለስ ተባበሩኝ እኔ Orthodox ነኝ ግን ብዙም ጠለቅ ያለ የሀይማኖት እውቀት የለኝም እና ከሰሞኑ እነዚህን ጥያቄዎች አይቼ ገረመኝ እናም መልስ ፍለጋ መጣሁ 1. ፈጣሪ የበደሏቹህን ይቅር በሏቸው ይላል ግን እኛ ሀጢያት ስንሰራ ለምን ይቅር ብሎ ገነት አያስገባንም 2. ፈጣሪ ለምን ህፃን ልጆች ሲወለዱ ሙሉ ጤናማ አያደርጋቸውም አካል ጉዳተኛ ልጅ ለምን ይወለዳል አመሰግናለሁ መልሱን ለማወቅ ፈልጌ ነው ፈጣሪ ከእንደዚ አይነት ፈታኝ ሰው ይጠብቃቹ
Dec 19, 20201 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” — ዮሐንስ 3፥16 “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” — ሮሜ 8፥34 2, “እርሱም፦ አንተ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀህ ብትሰማ፥ በፊቱም የሚበጀውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህም፤ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝና አለ።” — ዘጸአት 15፥26 “አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ።” — ዘጸአት 23፥25
Dec 19, 2020