Is there any open public library (Ye wereda library) in Addis? #URGENT
Dec 17, 2020ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሕዝብ ንባብ አገልግሎት መስጠት እጀምራለሁ አለ። አጀንሲው እነደተናገረው ከሆነ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እየተከላከለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቋል።በሕዝብ ንባብ ቤቱ ከአሁን ቀደም በአንድ ጊዜ ከ1000 በላይ አንባቢዎችን ያስተናግድ እንደነበር የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ዳይሬክተሩ አቶ ያሬድ ተፈራ ተናግረዋል።አሁን ግን ከግማሽ በላይ በመቀነስ 326 ሰዎች ይስተናገዳሉ ብለዋል።አንባቢዎች የተጠቀሙባቸው መጻሕፍትም ከ3 እስከ 5 ቀናት ከንክኪ ርቀው ተለይተው ይቆያሉ ተብሏል። ለዚሁ ሲባል 1 ክፍል ማዘጋጀቱን ነው ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ የተናገረው።የቤተ መጻሕፍቱ ተገልጋዮች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የንባብ አገልግሎት ማግኘት ትችላላችሁ ተብላችኋል።የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከልም ብርቱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ ሲልም ኤጀንሲው ጥሪ አቅርቧል።ለአጥኚዎችና ተመራማሪዎች ከነሐሴ 15፣ 2012 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱንም ተሰምቷል።ቀስ በቀስ ሙሉ የንባብ ቤቶቹን አገልግሎት ወደመስጠት እንደሚያሸጋግርም ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ እወቁት ብሏል። Via Sheger FM @YeneTube @FikerAssefa
Dec 17, 2020