ምን ላድርግ ? አንድ ምወደው ጓደኛየ አለ እና የሆነ ጊዜ ፍቅረኛ ነበረችው ። በጣም ነው ሚወዳት የነበረ ። የቤተክርስቲያን ሰው ነው ፍቅረኛውንም በተክሊል አግብቶ እሷ ጋር መኖር ነው ሚፈልግ የነበረ ። ግን ባለሰበው እና ባልጠበቀው ምክንያት ተለየችው ። በጣም ተጎዳ ፤ ከዛ በኋላ ሴት አላምንም አለ ፤ እና ብዙ ሴቶች ጋር ያወራል ። ባጋጣሚ አኔ ከሆነች ልጅ ጋር ፍቅር ጀመረኩ እና ከእህቷ ጋር ፍቅር እንደጀመረ አወቅሁ ። ሙሉ ማንነቱ ግን ደብቋታል ። እሷ ግን በደንብ አምናው የተወሰኑት ቤተሰቦቿ ያውቃሉ ። ትክክለኛ ማንነቱን ግን አያውቁም ። እሱ ደግሞ ምወደው ጓደኛየ ነው ። ልጅቷ እንድትጎዳም አልፈልግም ። እኔም አህት አለኝ እና ምን ላድርግ?
Dec 16, 2020በቅድሚያ እሱ የቅርብ ጓደኛህ እንደመሆኑም መጠን በደንብ ምከረው ፡ ወደቀድሞ ማንነቱ እንዲመለስ አበረታታው አግዘው ፡፡ ያንን አላደርግም ብሎ እሷን ሊጎዳት በሚችል ደረጃ አግባብ ያልሆነ ነገር ሲያደርግ ብታየው ግን እሷን አረጋግተህ ፡ ነገሩንም ቀለል አርገህ ለሷ ብትነግራት ባይ ነኝ ፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ምንም ቢሆን አንዱ ባጠፋ ሌላው መቀጣት የለበትም ፡ ይቺ ልጅ ጥፋት ስለሌለባት መጎዳት የለባትም ሲቀጥል እሱም ቢሆን ሌላ ሰውን ጎድቶ የበለጠ ህይወቱ ቢመሰቃቀልበት እንጂ ምንም አይጠቅመውም፡፡
Dec 17, 2020