Anonymous
#health
ሰላም ጓደኞቸ የጨነቀኝን ላካፍላቹ ወደድኩ እኔ አዲስ ሰው ለመቅረብ አይከብደኝም ተግባቢ ነኝ ችግሩ ከዛ በኋላ ሚመጣው ነው አዲስ ጓደኞች ተዋውቄ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን በሆነ ምክንያት ከተራራቅነ በስራ በትምህርት ወይም በሌላ እንደገና መቅረብ በጣም ነው ሚከብደኝ እንዴ የራቀኝን ሰው ስልክ መደወልም መቅረብም አልፈልግም ለምንድን እንደሆነ አላውቅም በተለይ አዲስ ያወኳቸውን አፍላ ልትሉ ትችላላቹህ ግን ደሞ ከነሱ ተለይቸ ሌላ ሰው ፈልጎ እስኪያገኘኝ ድረስ ብቻየን ብሆን ነው ደስ የሚለኝ ብቸኝነት ሳላበዛ አልቀርም መሰል ሀሳባችሁን አካፍሉኝ አመሰግናለሁ
Dec 15, 20203 engagements