በመጀመሪያ ብዙ ትያቄዎች በአይምሮዬ ውስጥ ተመላለሱ እንዲህ ነዉ ብዬ እንዳልጠይቅ ግራ ገባኝ ነገር ግን ለራሴ ያልገባኝ ጥያቄ በሌሎች ተጠይቆ ጥያቄዬን ካገኘሁ ብዬ ባነብም አጣሁት በዚህ የሀሳቤ ፀብ መሀል ለምን ተፈጠርክ ? ሀሳቡም ሲሰፋብኝ ሰውን ለምን መፍጠር አስፈለገ ? ከተፈጠረ በኋላም አዳም ተሳሳተ መልሶም ወደ ገነት ለመግባት ፈተናም ተዘጋጀለት በዚህ ሁሉ መሀል እኔ እንዴትም ሆነ እንዴት ወደዚህ አለም መጥቻለው የዚህንም ዓለም ምርጥ ፈተና ተፈታኝ ሆኛለው እና ማን እንደሆንኩም በትንሹ ገብቶኝ ብዙ ጥያቄዎች አሉኝ ????? ከጥያቄዬ አንዱ ፈጣሪ ወደዚህ ዓለም የሚመጣበት ቀን በመፅሐፍ ቅዱስ ተፅፏል ወይም ደግሞ በትንቢት ተናግረዋል ይህም ትንቢት ላይ በእኔ መምጫ ጊዜ ተብሎ የሚሰሩትን ሀጥያቶች ተፅፈውበታል እነዚህንም ሀጥያት የሚሰሩ ሰዎች እንደሚፈጠሩ ከሀሳቡ መረዳት ይቻላል እና እነዚህን ሀጥያት የሚሰሩ ሰዎች ሀጥያተኛ ይባላሉ ? ለትንቢቱ መፈፀሚያ እስከሆኑ ድረስ ባይፈልጉም የሚላበሱት ባህሪ አለ ማለት ነው?? ስለዚህ እኛ ሰዎች ማለት ከተፈጠርን በኃላ ነው ይችን ዓለም መቀላቀላችንን ያወቅነው ስለዚህ ኑሮአችንም እኛ ባልነው ሳይሆን እሱ በፈጠረን በፈጣሪያችን የተገደበ ነው ??? እኛስ የትንቢቱ መፈፀሚያ ከሆን እኛ በፈለግነው ሳይሆን በትንቢቱ በተባለልን መሰረት ነው ምኖረው? እኔ ይህን ጥያቄ ከማን መልስ እንደማገኝ ባላውቅም ግን በድፍረት አሁን ላናንተ አቅርቤዋለሁ
Dec 08, 2020I really enjoyed reading your question....what im about to say is not related to ur question but I want you to know that you have a writing skill bro, I feel like read a novel.
Dec 09, 2020