ወደ እግዚአብሔር በቀጥታ ብንፀልይ አይሰማንም ትላላቹ? ምክንያቱም መዝሙር 65 (Psalms) 2፤ ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል። በቅዱሳን መፀለይ እና በቀጥታ ወደ እግዚብሄር መፀለይ የቱ ነው ትርፋማው ዮሐንስ 16 (John) 23፤ በዚያን ቀንም ከእኔ አንዳች አትለምኑም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል። 24፤ እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፤ ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ለምኑ ትቀበሉማላችሁ። I want answer from bible only
Nov 21, 2020ሐዋርያው "...ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይፀልይ ። የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች ። /ያዕ 5:16/ ባለው ተረጋግጧል ። ቅዱሳንም ራሳቸው ሌሎች ሰዎች እንዲጸልዩላቸው ጠይቀዋል ። "...ስለኛ ጸልዩ " (2ኛ ተሰ 3:1 ) ለዕብራውያንም "ጸልዩልን በነገር ሁሉ በመልካም ሁሉ እንድንኖር (ዕብ13:18) በመጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ለሌላው እንዲጸልይ የተጠየቀበት ሁኔታ ብዙ ነው ። ታድያ ቅዱሳን እንድንጸልይላቸው እኛን ከጠየቁን እኛ ደግሞ እነርሱ ስለኛ እንዲጸልዩልን አንጠይቃቸውምን ? ገና በዚህ ዓለም በመንፈሳዊ ጦርነት ሳሉ ለመከራ የተጋለጡትን ቅዱሳንን እንዲጸልዩልን ከጠየቅን ተጋድሏቸውን የፈፀሙና በገነት ከክርስቶስ ጋር ያሉትን እንዲጸልዩልን አንለምናቸውምን ? ፡ሌላው #እግዚአብሔር_ሰዎች_የቅዱሳንን_ምልጃ_እንዲጠይቁ_ፈቅዷል ። እግዚአብሔር እራሱ የቅዱሳንን ምልጃ ጠይቋል ተቀብሏልም ። እንዲሁም ምልጃ እንዲቀርብ ሰዎችን ወደ ቅዱሳን ልኳል ። እስቲ ለዚህ ማስረጃ እናቅርብ ። " አባታችን #አብርሃም ሣራን እህቴ ነች ስላለ ንጉሱ አቤቤሜሌክ ሣራን ወደ ቤተ መንግስት ወሰዳት ።ጌታም ወደ አቤሜሌክ በህልም መጣ በሞትም አስፈራራው ። አሁንም የሰውዬውን ሚስት መልስ ነብይ ነውና #ስላንተም_ይፀልያል ትድናለህም ። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በእርግጥ እወቅ" ። /ዘፍ 20:7/ አቤሜሌክን እግዚአብሔር ሣራን እንደመለሰ ወዲያውኑ ሊምረው ይችል ነበር ። ነገር ግን ይቅር ይባልና በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር #የአብርሃምን ምልጃ ጠየቀ ። #የኢዩብ_ታሪክ ፦ "...በእግዚአብሔር ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንደ ባሪያዬ በአንተ በሁለቱ ባለንጀሮችህ ላይ ነድዶአል ። አሁን እንግዲህ 7 ወይፈኖችና 7 አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ዘንድ ሂዱ የሚቃጠልንም መስዋዕት ስለራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ #ስለእናንተ_ይጸልያል። እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለው ። /ኢዮ 42:7/ ከላይ ባየናቸው በሁለቱም ሁኔታዎች እግዚአብሔር ራሱ ለበደለኛ ሰዎች ተናገረ። ሆኖም ራሱ በቀጥታ ይቅርታን አላደረገም ። ነገር ግን የቅዱሳንን ጸሎት ጠየቀ። ይህም ቅዱሳን በሰዎች ፊት ይከብሩ ዘንድ ነው #ስለ_ሰዶም_የአብርሃም_ምልጃ አብርሃም ጉዳዩን ሳያውቀው እግዚአብሔር ሰዶምን ሊቀጣ ይችል ነበር ። አብርሃም በእግዚአብሔር ፈቃድ ጣልቃ አልገባም ። ነገር ግን ጌታ ለአብርሃም ስለ ሰዶም ምልጃን ያቀርብ ዘንድ ጉዳዩን ገለፀለት ። ምልጃውንም ተቀበለው ። አብርሃም በሰዎች ፊት ከፍ ከፍ ይል ዘንድና እኛም ስለቅዱሳን ክብር እንድንረዳ ይህ በመጽሐፍ ይጻፍ ዘንድ የእግዚአብሔር ፍቃድ ሆነ ። /ዘፍ18:17/ #ሙሴ_ስለእስራኤል_ምልጃን_እንዳቀረበ በወርቅ የሰሩትን የጥጃ ምስል አምልከዋልና እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያጠፋ ወደደ ይህንንም ለነብዩ ሙሴ አሳወቀው ፤ ስለ ህዝቡ ምልጃ እንዲያቀርብ ዕድል ሰጠው ከዚያም ምልጃውን ተቀበለው ። ልክ አብርሃም "እግዚአብሔርን እንዲህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ " እንዳለው ፤ ሙሴም " ... እግዚአብሔር በሕዝብህም በክፋታቸው ላይ ራራ አለ ..." እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ሊያደርግ ስላሰበው ክፋት ራራ ። /ዘጸ32:7/ እኛም ይህን አብነት አድርገን ቅዱሳን ይጸልዩልንና ይማልዱን ዘንድ እንጠይቃለን ።
Nov 23, 2020