What are z steps involved "nesha lmegbat"? In details
Nov 21, 2020ዋናው ቁምነገር ከልቦ ንስሐ ለመግባት መወሰኖት ነው። ተግተው እግዚአብሔር በምሕረት እንዲመለከቶ ይጸልዩ። ከዛ በአከባቢዎ ካለ ደብር ሄደው የመረጡትን ካህን የንስሐ አባት እንዲሆኖት ይጠይቁ። ከዚያም ከርሳቸው ጋር ምንም ሳይደብቁ የልቦን ይወያዩ። ኀጢአቶትን ብቻ ሳይሆን የሚያሳስቦት ነገር ካል ስለ ስራዎ ስለ ፍቅር ሕይወቶ ስለ መንፈሳዊ ሕይወቶ ብቻ እርሶን በተመለከተ ያለውን ነገር ሁሉ ይንገሯቸው። በአንዴ መነዘዝ ሊከብድ ይችላል ስለዚህ እስክትላመዱ የሚያስጨንቆትን ነገር በመንገር አልያም ባንዳንድ ነገሮች ላይ ምክር በመጠየቅ እርሳቸው ብዙ እንዲናገሩ እድል ይስጧቸው። ከዚያ ከተናዘዙ በኋላ ቀኖና ይሰጦታል እርሱን እንደተባሉት ከፈጸሙ በኋላ ለርሳቸው አሳውቀው ወደ ቅዱስ ቁርባን ይቀርባሉ😊። ለተጨማሪ ጥያቄ በውስጥ መስመር ያናግሩኝ
Nov 21, 2020