✔️መች ነዉ እርዳታ መጠየቅ ያለብን ?
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች ቢያንስ ለሁለት ሳምንት ያክል እራስዎት ላይ ካዩ እርዳታ መጠየቅ ይኖርብዎታል። በማንኛውም ጊዜ እራስዎን የመጉዳት ወይም ራስን የማጥፋት ስሜት የሚሰማዎት ከሆነ በአስቸኩአይ እርዳታ ያግኙ ።
✔️የት ነው እርዳታ መጠየቅ ያለብን ?
የሚቀርቡት እና ልያናግሩት የሚችሉት የ ቅርብ ጓደኛ ወይም ዘመድ ካለ እርዳታ ለማግኘት ለመጠየቅ አይፍሩ ; በቀጣይነት ግን ሁልጊዜም የ ስነ አእምሮ ሕክምና ባለሙያ እገዛ ማግኘት ይኖርብዎታል ።
የድብርት ህመምን እንዴት መቋቋም ይቻላል
✔️መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ ንቁ ለመሆን ይሞክሩ
✔️ከቤተሰብ / ጓደኞች ጋር ይገናኙ – መገለል ድብርትን ያባብሳል። ጊዜ ይፍጠሩ እና ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ይገናኙ በአካል ካልተቻለ በስልክ ያግኙ። ከጓደኞችዎ ወይም ከቤተሰብዎ ጋር ጠንካራ ትስስር ይፍጠሩ።
✔️የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ይምረጡ – በጣም የሚወዱትን እና ስሜትዎን ሊያሻሽል የሚችል ነገር ለማድረግ ይጣሩ ለአብነት፦በተፈጥሮ ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ያሳልፉ ፣ የቤት እንስሳትን ይንከባከቡ ፣ በጎ ፈቃድ ስራዎች ይስሩ ፣ ይደሰቱበት የነበሩትን የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ (ወይም አዲስ መዝናኛ) መርጠው በመተግበር ጭንቀትዎን ይቀንሱ። ከሚያምኑት ሰው ጋር በመሆን በመልመጃዎች ወይም በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችዎ በመሳተፍ እና ደስ ሊያሰኝዎት በሚችሉ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ ጭንቀትን መቀነስ ይችላሉ ፡፡
✔️በቂ እንቅልፍ ለማግኘት ይሞክሩ – እንቅልፍ እና ስሜት በቅርብ የሚዛመዱ እንደመሆናቸው ጥሩ እና በቂ እንቅልፍ ለማግኘት ይሞክሩ፡፡ በአልጋ ወይም ሌላው ቀርቶ በመኝታ ክፍልዎ ውስጥ ሥራ መሥራት ከመዝናናት ይልቅ አልጋዎን ከጭንቀት ጋር እንዲያዛምዱት ሊያደርግ ስለሚችል ለመተኛት ብቻ አልጋዎን ይጠቀሙ።
✔️በጣም ወሳኝ የሆኑ የህይወት ውሳኔዎችን እስኪሻልዎት ያራዝሙ
✔️ከባድ ስራዎችን ወደ ትናንሽና መስራት ወደሚችሉት መጠን ይከፋፍሉ ፣ ቅድሚያ መሰጠት ያለባቸው ስራዎች ይለዩ እና የሚችሉት ያክል ብቻ ይስሩ
✔️እራስዎን በእራስዎት በመጠጥ ወይም በባለሙያ ባልታዘዘ መድኃኒት ለማከም አይሞክሩ።
✔️ዋቢ መጽሐፍ
David G.Myers, 2010, Psychology, 9th Ed. Diagnostic and statical manual of metal disorders , 5thEd G.E.Stelmach & P.A.Varoon, Advances in psychology 21, The self in Anxiety stress and depression , Edited by Ralf Schewazer https://t.me/joinchat/AAAAAFb-KZCR_5RFvfyjAA
Nov 09, 2020