How can I overcome my extreme shyness when meeting new people specially Men?
Nov 08, 2020Why do you feel shy?
Nov 09, 2020How can I overcome my extreme shyness when meeting new people specially Men?
Nov 08, 2020Why do you feel shy?
Nov 09, 2020that's also ma question , am a boy ena meeting girls is really hard for me specially the eye contact thing 🤦♂️
Nov 09, 2020✉️✉️✉️✉️ በራስ መተማመን ✉️✉️✉️✉️ ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡ ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡- 1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡ 2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡ 3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡ በዚህም ከሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ፣ ስትሳሳት ይቅርታ ለማለት እና የማይሆን ነገር ሲመጣ ወይም ስትጠየቅ በአክብሮት አይሆንም ለማለት አትፍራ፡፡ ሁልጊዜም ከዚህ በፊት ያሳካሃቸውን ነገሮች እና ጠንካራ ጎኖችህን አስባቸው፡፡ 4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ ካልሆነ ደግሞ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ነቀፌታቸውን ተመልከት፡፡ ለዚህ እንዲረዳህ ደግሞ የተወሰነ ጊዜ በመውሰድ እነዚህን ሰዎች እና ድርጊቶች ለይተህ አውጣ፡፡ 5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡ ተጨማሪ የሆኑ ጊዜህን የምታሳልፈበትና ስኬታማ የምትሆንበትንም ነገሮች እግረ-ሃሳብህን ለይተህ አውጣና ትኩረትህን ስጠው፡፡ 6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡ ከሰዎች ጋር ባለህ መልካም፣ ግንኙነት፣ አዳማጭ በመሆንህ፣ የሰውን ችግር መረዳት በመቻልህ፣ ውጥረትን በመቋቋም ብቃትህ ፣ እስካሁን ባሳካሀቸው ስኬቶችህ እና በመሳሰሉት ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ በማድረግ ኩራትህን ጨምር፡፡ 7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡ ስለ ራስህ መዋሸት በወቅቱ ጥሩ ስሜት ሊፈጥርልህ ይችላል ሆኖም ግን ወዳጄ ጊዜው ባለፈ ቁጥር እውነቱ ከዛሬ ነገ ወጣ በማለት በስጋት እንድትኖርና ሁሌም በእራስ በመተማመን እና በልበ ሙሉነት እንዳትቀርብ ያረግሃል፡፡ በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡ ሰላማችሁ ይብዛ………. ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
Nov 09, 2020* think as you are likeable * learn social skills * be confident and focus on your positive character * dont be obsessed by your every little detail even others might not notice. * no one is there to judge u but to talk and have a mutual convo. i.e others are as concerned as you are and you should not fear. * socialize in school, fam gatherings, sports and see how easy it could be to meet complet strangers...it is fun, no fear no shyness
Nov 09, 2020I have a cure. ስንት ትገዣለሽ😅😅
Nov 09, 2020think like they are goats
Nov 09, 2020What😁
Nov 10, 2020Ask for my identity
Nov 09, 2020