ከሦስት አመት በፊት አብሬው የነበርኩት ልጅ ነበር። እኔ አልወደውም ነበር ግን ግንኙነቱ ለእኔ አስፈላጊ ስለነበር ነው አብሬው የሆንኩት። እና ከአንድ አመት በኋላ ተለያየን። ከዛ ከሁለት አመት በኋላ በቴሌግራም ማውራት ጀመርን። እናም በደምብ ማውራት ከጀመርን በኋላ እንደሚወደኝ ነገረኝ፣ እኔ ግን እንደማልወደው እና አብሬው መሆን እንደማይችል ነገርኩት። ከዛ በየቀኑ እንደሚወደኝ እና እንደሚጠብቀኝ ይነግረኝ ነበር ። እኔም እንዳይጎዳ በሚገባው በመንገድ ላስረዳው ሞከርኩኝ ፣ ግን አልተሳካም። ከትንሽ ጊዜ በኋላ እየተጫወተብኝ እንደነበር ነገረኝ። ባልወደውም በጣም አናዶኝ ነበር ። ከዛ የሡ ጓደኛ ከእኔ ጓደኛ ጋር አብረው ሆኑ። ከዚ በፊት አብረው ነበሩ እናም በመሀል ተጣልተው ነው። የሱን ባላውቅም ጓደኛዬ በጣም ነው የምትወደው። ግን እኔ እንደ ጓደኛው ሆኖ እሷንም እንዳይጎዳት ፈርቻለው።በቻልኩት መጠን አስጠንቄያታለው። ግን ሙሉ ለሙሉ ልታምነው ስለምትፈልግ እውነት እንደሚወዳት እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ ? አመሰግናለሁ
Nov 08, 2020ከፅሁፍሽ የተረዳሁት ልጁ በጣም ውሸታም እንደነበረ ነው። አምነሺው ነበር። ውሸቴን ነው ሲልሽ ደነገጥሽ። ውሸቴን ነው ያለው ውሸቱን ቢሆንስ? ለሰዎች ተናግረሽ እንዳታሳፍሪው ቢሆንስ?-- ምክንያቱም አንቺ አትወጂውም ነበር። ጓደኛሽ የራሱዋ አእምሮ የላትም?-- ለምን ጠረጠርሽው ጓደኛዋን? የዛኛው 'ውሸቴን ነው' ማለት አስደንግጦሽ ነው ወይስ ትክክለኛ መረጃ አለሽ?-- ምን አልባት ግንኙነታቸው ለጓደኛሽ አስፈላጊ ቢሆንስ?-- አንቺም ከማትወጂው ሰው ጋር ለአንድ አመት አሳልፈሻል እና.....
Nov 09, 2020