ከቀናቶች በፊት ከሰፈር ልጆች ጋ ስለ TPLF ድንገት ወሬ ተነሳና ትግሬ ማለት ብለው ወሬ ጀመሩ እኔም ገርሞኝ ሁሉም ትግሬ አንድ አይደለም ብየ ልከራከር ገና ሀሳቡን ሳነሳ ጭራሽ ሊሰሙኝ ፈቃደኛ አልነበሩም ከሁሉ የገረመኝ ከሰፈር ቦዘኔዎች ይሻላል ያልኩት አባቴ የነሱን ሀሳብ መድገሙ ነው እኔ ደሞ ይህንን ልል የቻልኩት እኔ የጎንደር ልጅ ነኝ በጣም ደግ የሆነች የትግራይ ተወላጅ ስለማውቅ ነው በጣም ጥሩ ጓደኛየ ናት ሁሉም አንድ አይደለም ብየ እንድደመድም አድርጋኛለች እናንተስ ምን ታስባላቹ ይሄ ጥላቻ እንዴት ሊቆም ይችላል።
Nov 06, 2020ልክ ነህ, ወንድሜ። ሁሉም ትግሬ በፍጹም አንድ ሊሆን አይችልም። የዚህ ሁሉ ጥላቻ እና በደል መንስኤው መርዘኛው የሌቦች ስብስብ ህወሃት ነዉ። ግን ብዙ አትጨነቅ, ወንድም። ይህ ቆሻሻ ቡድን በጣት የሚቆጠር እድሜ ነው የቀረው። ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አፈር ከድሜ ያስገባዋል። በመጨረሻም ኢትዮጵያችን ሠላም ትሆናለች። 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Nov 07, 2020