I'm national exam taker ena I'm natural science student anyone tell me which one is more difficult from what subject should I start studying and any study tips please🙏🤷♀
Nov 03, 2020የምትችያቸውን(ሚቀሉሽን) ቀጥቅጠሽ አንብቢ። ሦስትም አራትም ይሁኑ። ከዛ ቀጣይ መካከለኞቹን። ከዛ ምንም ማትችይውን። ቡዙ ግዜሽን መስጠት ያለብሽ ለምትችይው ትምህርት ነው። የጥናት ፕሮግራም አውጪ። እራስሽን ከሶሻል ሚዲያ ፣ ከተራ ወሬ እና ከቲቪ አርቂ። ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን የሆነ ያህል። የቀድሞ ፈተናዎችን ስሪ። የማይገባሽን ከሌሎች ተማሪዎች ከመረዳት ወደ ዃላ አትበይ። የተረዳሽውንም ከጠየቁሽ አስረጂያቸው ፣ ለራስሽም እንደ ክለሳ ነው። ስታጠኚ ያነበብሺውን በራስሽ ቃላት ወረቀት ላይ ለመግለፅ ሞክሪ። ፃፊው። ከዛ ከመፅሃፉ ጋር አስተያዩ። ስህተት ካለው ደግመሽ አጥኚ። ደጋግመሽ ማጥናትሽን አትርሺ። እስፖርት ስሪ። የሚያስደስትሽን ነገር በትንሹ አድርጊ።
Nov 04, 2020