ሠላም☺️ መጀመሪያ አላውቀውም ነበር እሡ ግን ያውቀኛል፡፡ከዛም ለፍቅር ጠየቀኝ እንደማይሆን እንደ እህትናወንድም እንድንቀጥል ነገርኩት ምክንያቱም አዲስ ተማሪ ነበርኩ እና ስለኛ ቤተሠብ በደንብ ያውቃል ፡፡እናም ት/ቴ ላይ ማተኮር እንደነበረብኝ አምን ነበር፡፡ከዛም ትንሽ ሳልቆይ ተሸነፍኩ እኔነቴን ተቆጣጠረው፡፡ማንንም ዞር ብዬ የማላይ ልጅ ተበላሸሁ፡፡ከዛ አዲስ ተማሪ ስለነበርኩ ብዙ ነገር አላውቅም ስለ እሡ፡፡እናም ከኔ መሸሽ ከ 10ሴት ጋር ሲንዘላዘል ሳየው ቆረጠልኝ፡፡እናም በወደድኩት ሠዓት ብዙ ነገር አድርጌ ነበር ፡፡እናም ከልብሽ እንደ ምትወጂኝ ተረዳሁ ብሎ ይቅርታ ጠየቀኝ ግን እንደ ቀድሞ አልሆንኩለትም ነገር just friend እንዲሆነኝ ነበር የፈለኩት እና ድንገት በምናወራበት ሠዓት አልተግባባንም፡፡እናም አንቺን ማናግረው ለአንቺ ስል ነው እንጂ ፈልጌ አይደለም ተገድጄ ነው አለኝ ጥዩው ሄድኩ እናም አልተላሁትም ግልጽ ስለተናገረ ጥሩ ነው ብያለው ግን ለኔ ምንም ክብር እንደሌለው አምኛለሁ፡፡ከዘጋሁት አንድ ወሬ ሆነ በየቀኑ ይደውላል text ያረጋል፡፡እናም ጥፋቴ አልገባኝም ይላል እኔ ለሡ ሆነ ስለ ፍቅር አላስብም ማሠብም አልፈልግም፡፡ግን ማኩረፍ የለብኝም ማለት ፀሎት ስፀልይ ሁሌ ትዝ ይለኛል፡፡ይቅር ማለት አለብኝ ብዬ አምናለው፡፡፡፡ነገ ልደቱ ነው እና ላናግረው?ምን ብዬ ላናግረው?ተባበሩኝ 😊
Nov 03, 2020ኸረ ትረካውን ወድጄ እያነበብኩ ሳላውቅ ቁርጥ አለብኝኮ...የምር አፃፃፍሽ ደስ ሲል...እና ደሞ ፀሎት ስፀልይ ያልሽው ምናለ ሁሉም ሰው እንዳንቺ በሆነ...ልቤን ነካሽው...ብቻ hbd በይው...ይቅርታ እንዳደረግሽለትም ንገሪው። ላንቺም ለሱም እረፍት ነው። ግን ስታወሪ እሱን እንደምትፈልጊ አይነት አትሁኚ። ተመልሶ ቀብረር እንዳይል።
Nov 03, 2020