የሰው ልጅ መኖር የሚፈልገው አለመኖርን ስለሚፈራ ነው። አለመኖርን ደግሞ በሶስት መንገድ ማጥፋት ይፈልጋል አንደኛው የፅድቅን መንገድ በመፈለግ ከአምላኩ ጋር ታርቆ የከሞት በኃላ የዘላለም ህይወትን ማግኘትን ይፈልጋል ሁለተኛው ደግሞ የአብራኩ ክፋይ የሆነን ልጅ በመውለድ ዘላለማዊነቱን በልጁ ማስቀጠል ይፈልጋል ሦስተኛው ደግሞ በምድር ላይ እያለ ታላላቅ ስራዎችን በመስራት እሱ እንኩአን ባይኖር ስሙ ዘላለም እንዲኖር ይፈልጋል ስለዚህ እላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች የሰው ልጅ በምድር የሚኖርበት አላማ ሆነዋል። ከአለመኖር መፅሐፍ እንደተረዳሁት።ጥያቄዬ ምንድን ነው በርግጥ ህይወት ስለ እኔ እና ስለ እኔ ብቻ ነውን? ከእኔ ባለፈ ስለ ሌሎች አለመኖር ማሰብ የምንጀምረው መች ነው? መልሳችሁ በኢትዮጽያዊያን ቋንቋ ይሁን ምክንያቱም የኛ ስለሆነ።
Nov 03, 2020Ur name is in English bruh
Nov 03, 2020