ቆይ ኢትዮጲያዊ ሆነን እንዴት ሃይማኖተኞች ሆንን??? የምሬን ነው። ግራ ነው የሚገባኝ። አብሮ አደጌ ሙስሊም ነው። እኩዮች ነን። አባቱ ሼክ ናቸው። በጣም የታወቁ። ጓደኛዬም የአባቱን ፈለግ ከልጅነቱ ጀምሮ እስካሁን ይከተላል። ፕሮቴስታንት ጓደኞችም አሉኝ። እኔ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ቤተሰቦች አሉኝ። እስከ አስራ አምስት አመቴ ጥሩ አማኝ ነበርኩ። ጥያቄዬ ጓደኞቻችን ሌላ ሃይማኖት(ሙስሊሙ ኦ.ክርስቲያን ወይም ፕሮቴስታንት ፣ ፕሮቴስታንቱ ሙስሊም ወይም ኦ.ክርስቲያን) ..የተለያየ ሃይማኖት ኖሮን ሁላችንም ሃሴትን እያገኘን ከሆነ ፣ አእምሯችን ሃይማኖቶች ውሸት ሊሆኑ እንደሚችሉ ለምን መጠየቅ አቃተው???(የሁላችንም ሳይሆን የአብዛኞቻችን).. ሃይማኖት ከባህላችን ጋር ጥልቅ ቁርኝት ስላለው ይሁን? የኛ ሰዎች ከሃይማኖታቸው ውጪ መኖር እንደሚችሉ ሊመጣላቸው ይችላል??? ደሞ ብዙዎቻችን የእውነት አማኞች ነን? ሃይማኖትን ለማህበራዊ ህይወታችን(በዓል ለማክበር[ፌሽታ ፣ መጠጥ ፣ አዳዲስ ልብስ ወዘተ ወዘተ]) እና ለስኬት ብቻ ምንጠቀመው አይመስላችሁም???? ምን ያህሉ ነው እውነት የሃይማኖት ህጎቹን ምንም ሳያቅማማ የሚከተለው??*ሰይጣን አሳሳተኝ እያለ ሚዘርፍ ፣ ሚያመነዝር ፣ ሰው የሚያማ[በጣም ጥሩ የሚባሉ ትልልቅ እናቶችን ጨምሮ] ፣ የሚቀና ፣ የሚመቀኝ አይበዛም??? Be Reasonable when u answer.
Nov 03, 2020Wendme ante sitet nachew yalkachew negeroch hulu tikiklegna nachew yale sew yelem demo ehen tiyaqe kemeteyekik befit ante silemitiketelew eminet mn yahl tawikalek?
Nov 03, 2020