እሽ፤ ባለፈው ሳምንት የ"laptop fan" ተበላሽቶ ከጓደኛዬ ጋር ልናሰራው መገናኛ ወሰድኩት። ከዛ እንዲሁ አየት አረገውና ምን እንደተበላሸብኝ ጠየቀኝ። እኔም "fan'ኡ ነው ያስቸገረኝ" አልኩት። እሱም :- "በቃ አታስብ ቀላል ነገር ነው። ከሳምንት በኋላ መምጣት ትችላለህ" አለኝ። እኔም ለጠቀ አድርጌ " ግን ወንድሜ ምንም file እንዲጠፋብኝ አልፈልግም እሽ!" አልኩት። እናላችሁ ጓደኛዬ ስራው እዛው አካባቢ ስለነበር ይዞልኝ መጣ። በጣም ጓጉቼ ፊቴ ላይም ደስታ እየተነበበ ስከፍተው (ወፍ laptop'ኡ ምንም ነገር አልነበረውም። Fan'ኡን ፅድት አርጎ ነው የሰራው፤ ለሱ አመሰግነዋለሁ። ግን ምን ልበላችሁ በቃ ፉርምትምትምት አድርጎ ነው የፎረመተው። እና ጥያቄዬ "format የተደረገ laptop reset ወይም back-up ማድረግ ይቻላል ወይ?" ነው። ያው ነገ ከነገ-ወዲያ መሄዴ አይቀርም። ግን ዝምብዬ በባዶ ሜዳ ከምጮህ format ማድረግ ከተቻለ ልሄድ፤ ካልተቻለ ደግሞ በቃ....😭 ቁርጤን ለማወቅ ነው። ጥያቄዬን ዝጋችሁ ያነበባችሁ፤ መልስ ለመመለስ ያሰባችሁና ወደፊትም ለምትመልሱልኝ የዚህ ቡድን ጓደኞቼ ከወዲሁ አመሰግናለሁ። መልሳችሁንም በጉጉት እጠብቃለሁ!!!🙏🙏🙏
Oct 31, 2020bruh couldn't you just ask with out the story 😂😂🤦🏽
Nov 01, 2020