Guys esti lejerba hmem yemihon meftehe kalachu sitash smet yelewm betam techegriyalew
Oct 30, 2020✍️ #በጀርባና #በወገብ #ህመም #ውሎዎት #እየተስተጓጎለ #ነው? 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 ♥♥#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን♥♥ ⏩ #የተከበራችሁ የገጻችን ቤተሰቦች የጀርባ አጥንታችን እጅግ ጥንቃቄን የሚፈልግ እና ጉዳት ያጋጠመው እንደሆን አጥንቱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአካል ክፍሎችም ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ጀርባን ብቻ የሚያምም ከሆነ ብዙውን ጊዜ ይሄ የዲስክ መንሸራተት ሳይሆን ይልቁንም የጀርባ አጥንቶች መገናኛ ላይ ያለ ችግር ሊሆን ይችላል። 👉 በዕድሜ ምክንያት ሊያጋጥም የሚችለው የጀርባ ሕመም እንዳለ ሆኖ ከባድ ዕቃ በምናነሳበት ጊዜ መጠንቀቅ እንዲሁም ቅጥ ያጣ ውፍረትም ሌላው መንስኤው በመሆኑ እሱን ማረም የግድ ይሆናል፡፡ 👉 የጀርባ አጥንቶች መላው ሰውነታችንን ተሸከመው ከመያዛቸውም በላይ የእያንዳንዳችን አቋቋም አካሔድ፣ አቀማመጥና አተኛኘት ይወስናሉ፡፡ በዚህ የሠውነታችን ክፍል ላይ የሚደርስ ጉዳት ለብዙ የጤና ችግሮች መንስኤ ለሆነው ችግርና ለጀርባ ህመም መነሻ ምክንያት ይሆናል፡፡ የጀርባ ህመም በጀርባ አካባቢ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን ቀስ በቀስ ወደ አንገት፣ እጅ፣ እግርና ወደ ፊኛ አካባቢ በመተላለፍ የችግሩ ተጠቂ የሆነው ሰው እንደልቡ ለመንቀሳቀስ፣ ዕቃ ለማንሳትና እንደፈለገ ለመዟዟር እንዳይችል ያደርጉታል:: 👉 በጀርባ ህመም መንስኤነት የሚጠቀሱ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ከእያንዳንዱ ሰው የዕለት ተዕለት ተግባራት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያላቸው ጭንቀት፣ ድብርትና የሥራ ጫና የጡንቻ መወጣጠር እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ በጀርባ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችና ነርቮች እንዲኮማተሩ ያደርጋል፡፡ በዚህ ሣቢያም ከቀላል እስከ ከባድ ደረጃ ያላቸው የወገብ ህመሞች ይፈጠራሉ፡፡ 👉 ከዚህ በተጨማሪም ለወገብ ህመም በዋነኛ መንስኤነት ከሚጠቀሱት መካከል የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸው፡- 📌 የጨጓራ ህመም፣ 📌 የዲስክ መንሸራተት፣ 📌 የአፈጣጠር ችግር፣ 📌 የአካሄድ፣ የአቀማመጥና የአተኛኘት ችግሮች፤ 📌 የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ 📌 የምግብ መፈጨት ሥርዓት መስተጓጐል፣ 📌 ጡንቻዎችን በአካላዊ እንቅስቃሴ አለማጠንከር፣ 📌 የኩላሊት፣ የማህፀን፣ የዳሌ፣ የሪህና የስኳር በሽታዎች እንዲሁም የጨረር ህክምናዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ 👉👉 የጀርባ ህመም ሲከሰት የተለያዩ ምልክቶች የሚኖሩ ሲሆን ምልክቶቹ እንደ የሰው ሁኔታና የበሽታ መከላከል ብቃት ሊለያዩ ይችላሉ ሆኖም የጀርባ ህመም ዋነኛ ምልክቶች እንደሆኑ ከሚታወቁት መካከል፡- 📌 ራስ ምታት የራስ ማዞርና መደንዘዝ፣ 📌 አንገት ለማዟዟር መቸገር፣ 📌 የእጅ መደንዘዝና እንደልብ አለመታዘዝ፣ 📌 ወገብ ላይ ቁርጥ የሚያደርግ ህመም መሰማት፣ 📌 የጡንቻዎች መወጣጠር ስሜት፣ 📌 ቁርጥማት፣ 📌 ሠገራና ሽንት መቆጣጠር አለመቻል፣ 📌 የእግርና የእጅ መሸማቀቅና እንደ ኤሌክትሪክ የሚነዝር ህመም ይገኝበታል፡፡ 👉ማንኛውም ሰው እነዚህን ምልክቶች በተደጋጋሚ ያስተዋለ እንደሆነ ወደ ባለሙያ ዘንድ በመሄድ ለችግሩ መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል፡፡ 👉👉 #ለጀርባ #ህመም #ከሚያጋልጡ #ነገሮች #መካከል #የሚከተሉት #ዋነኞቹ #ናቸው፡- 📌 በግዴለሽነት አካልን ያለ አግባብ በማጠማዘዝ፣ 📌 ከባድ ዕቃን ሰውነትን ከጉልበት አጠፍ ሳይሉ በቀጥታ አጐንብሶ ለማንሳት መሞከር 📌 ተንሸራቶ በወገብ መቀመጥና 📌 በመኝታ ጊዜ በጀርባ ተንጋሎ መተኛት 📌 ወንዶች ከኋላ ኪሳቸው ውስጥ ተለቅ ያለ የኪስ ቦርሳ ይዘው ሲቀመጡ፣ በዳሌ አጥንታቸው ላይ መዛባትን በማስከተል ለጀርባ ህመም ይዳርጋቸዋል 👉👉 #የጀርባ #ህመም #ህክምናው #ምን #ይመስላል? 👉 ከመድሃኒት ህክምና ሌላ በሙያተኛ የታገዘ ጅምናስቲኮች፣ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚሰጡ ፊዚዮቴራፒዎች፣ የአኮንፓክቸር ህክምናዎች ለወገብ ህመም ህክምና ይረዳሉ፡፡ ማንኛውንም አይነት ህክምና ለማድረግ ከመሞከር በፊት ግን የህክምና ባለሙያን ማማከርና ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ 👉የአከርካሪ አጥንት በአደጋ፣ በመውደቅና መሰል በሆኑ ችግሮች ጉዳት በሚደርስበት ወቅት፣ ለተጐዳው የአከርካሪ ክፍል ድጋፍ በማድረግ በደረቅ አልጋ በማስተኛትና መድሃኒት በመስጠት፣ የአከርካሪ አጥንቱን ማከም ይቻላል፡፡ በአከርካሪ አጥንቱ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ከሆነና ህብለሰረሰር ድረስ የደረሰ ከሆነ በዚህም ሳቢያ እጅና እግር ከሰነፉ ብሎም መንቀሳቀስ ካቆሙ በቀዶ ጥገና መፍትሔ ያገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዲስክ መንሸራተትና በትርፍ አጥንት መብቀል ምክንያት የሚከሰተው የጀርባ ህመምም በቀዶ ጥገና ሊስተካከል ይችላል፡፡ ከላይ በዝርዝር ከተገለፁት ውጪ በሆነ የህክምና ዘዴ ማለትም በካይሮፕራክቲክ ህክምና ዘዴ ለአከርካሪ አጥንት ችግሮች መፍትሔ ማግኘት ይቻላል፡፡ 👉ከእያንዳንዱ ሰው የዕለት ተዕለት ተግባራት ጋር በእጅጉ ቁርኝት ያለውን የአከርካሪ አጥንት የጤና ችግር ከዚህ በታች ለመዘርዘር በሞከርናቸው መንገዶች ልንከላከለውና ለወገብ ህመም ከሚደረገው ችግር ልንድን እንችላለን፡፡ 📌 ከባድ እቃዎችን አለማንሳት 📌 በጀርባ አለመተኛት፣ 📌 በጐን በኩል መተኛትን መልመድ 📌 ውፍረትን መቀነስ 📌 ሲጋራ አለማጨስ 📌 አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ 📌 የሥራ አካባቢን ምቹ ማድረግ 📌 የተመጣጣነ ምግብ መመገብ 📌 ለረጅም ጊዜ አለመቆምና አለመቀመጥ 📌 የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እረፍት እያደረጉ ማሽከርከሩን ልማድ ማድረግ 📌 ሁልጊዜም በምንቀመጥበትም ሆነ በምንራመድበት ወቅት ቀጥ ብለን መሆን ይኖርበታል! መልካም የጤና ጊዜ!!! 👉👉 እርሶስ ይህ ችግር ተከስቶቦት የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎት ላይ ጫና ተፈጥሮቦታል ወይም ከዘመድ ወዳጆት ይህ ችግር የገጠመው አካል አለ? እንግዲያውስ ወደ 8809 ይደውሉ የባለሙያ ምክር ያግኙ!! 👉👉 ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!! (#በጤና #ባለሙያ #ቤተልሄም)
Oct 31, 2020