admins please prove My nose is bleeding(neser) dayly also mid night What is that helpppppp
Oct 30, 2020❤️ሰላም ለክሙ አበውየ ወእማትየ አሓውየ ወአሓትየ አነ ውእቱ መምህረ ፍካሬ ጥበብ ❤️ 🌱ዛሬ ስለነስር የተወሰነ ነግሪያችሁ ወደ መፍትሔው እንገባለን። #ነስር (የአፍንጫ መድማት ) በአፍንጫ ደም መፍሰስ (ነስር) የምንለው አስደንጋጭ የሆነ ነገር ግን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የህመም አይነት ነው ፡፡ አፍንጫ በጣም ውስብስብ የሆኑ የደም ስሮች ያሉበት የአካል ክፍል ከመሆኑም በላይ ለአደጋ በሰፊው የተጋለጠ ነው ፡፡ ነስር በሁለት ይከፈላል 1-ከፊተኛው የአፍንጫ ክፍል የሚመጣ (Anterior Nose Bleeds) ይህ አይነቱ የነስር አይነት ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር አይነት ምክንያት ነው ይህን ነስር በቀላሉ መቆጣጠር ወይም ማቆም ይቻላል ፡፡ 2-ከሗላኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nose Bleeds) ይህ አይነቱ የነስር አይነት በአብዛኛው በእድሜ በገፉሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን ከሌላኛው የተለየ ህክምና የሚያስፈልገው ነው፡፡ የአፍንጫ መድማት መነሻ ምክንያት -በአፍንጫ ውስጥ ባለ ድርቀት እና መሰንጠቅ -የደም ግፊት መጨመር ጋር በተያያዘ የሚመጣ -በአፍንጫ ላይ ከውጭ የሚከሰት አደጋ ወይንም አፍንጫ በመጎርጎር ምክንያት -በተለያዩ የህመም ወይንም መድሀኒቶች ምክንያት ደም መርጋት አለመቻል -የአየር ቶሎ ቶሎ መለዋወጥ የሚታይበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች -በቤተሰብ የዘር ሀረግ መሀል ተመሳሳይ ችግር ካለ -በተዋሲያን መጠቃት -የአልኮል እንዲሁም የሲጋራ ሱሰኝነት የአፍንጫ መድማት ለማቆም የሚረዱ መንገዶች -ከ30-45 ዲግሪ በማዘንበል (ጎንበስ ማለት)እረፍት ማድረግ ፤ጭንቅላትን ወደላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ ከማምጣት ባለፈ ጥቅም የለውም -2ቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራጣትዎ እና በጠቋሚ ጣትዎ ግጥም አድርጎ ለ10ደቂቃ ይዞ ማቆየት -በአፍ የሚወጣን ደም መትፋት -ከባድ ነገሮችን ጎንበስ ብሎ ለማንሳት አለመሞከር -አለማጨስ -ነስሩ ከአቆመ በሗላ አፍንጫዎትን አለመነካካት -ደም የሚያቀጥኑ የመድሀኒት አይነቶችን አለመጠቀም (ግድ ከሆነ የህክምና ባለሙያዎችን ምክር ማድረግ) -በሀኪም ትእዛዝ የሚታዘዙና አፍንጫን ሊያለሰልሱ የሚችሉ የቅባት አይነቶችን በአግባቡ መጠቀም -ቢያንስ ለ24 ሰአታት ያህል ሞቅ ያሉ መጠጦችን አለመጠቀም። ይህን በማድረግ ልንጠነቀቀው እንችላለን ነገር ግን በአጋጣሚ ነስር ቢመጣ የብሳና ዛፍ ከብሳና ላይ ፯ ጫፍ በመቁረጥ በእጅ በደንብ ካሹት ቦሀላ በአፍንጫ ማሽተት እና መወተፍ ነስሩ እንዲቆም ያደረግዋል። ።።።።።።።።ፍካሬ ጥበብ።።።።።።።።።።። ሼር በማድረግ በዚህ ህመም ለሚሰቃዩ እንዲሁም ግንዛቤ ለሌላቸው ወገኖቻችን እኛም እንጠቀምበት የእለቱ ምክሬ ነው።
Oct 30, 2020