Selam Simugnima fkr leinate minidin newi? Ine befkr minim lamin alichalikum Bizu sewoch liyasaminugn yitiralu ine gin duzz salihon alikerim mesel isikahun fkr mibal neger yelem bay hugnalew Isti inate asiredugn bigebagn Ameseginalehu
Oct 30, 2020💃የከንቲባው ልጅ 🕺 : ምዕራፍ ፫/3 ❤️ ክፍል ፳፱/29 ከአንዱ ምግብ ቤት ገብተን ምሳ ከበላን በዋላ "ፍቅር ግን ለአንተ ምንድነው...?" አለችኝ የከንቲባው ልጅ በልጅቷ የቅድሙ መልስ እንደኔው ተገርማ ። 'እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም ብያንስ አንድ ጊዜ አፍቅረናል ። እንደውም አብዛኞቻችን የፍቅርን ትርጉም ሳናውቅ ነው ያፈቀርነው ። anyways ፍቅር ግን ለኔ ...! አንድ ወንድና ሴት ተፈላልገው የሚመሰርቱት ግኑኝነት ...? ፡ እሱ ነው ፍቅር ...? ፡ አይመስለኝም ። እስቲ ወይ የራስሽን ወይንም ደግሞ የጓደኛሽን የፍቅር ታሪክ ለትንሽ ደቂቃ አስቢው ። እያሰብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ ። እርግጠኛ ሆኜ የምነግርሽ እራሳችንን ወደን እንጂ ሰውን አፍቅረን አናውቅም ። እንዴት...? ለምትዪኝ :- በመጀመሪያ ወንድ ከሆነ አንዲት ሴትን ፡ ሴት ከሆነች ደግሞ የሆነ ወንድ ፡ በሆነ አጋጣሚ ያገኛሉ ። የሆነ ነገሯ ይማርከዋል ፡ #90% መልኳ ፣ አካሄድ ፣ አለባበስ ፣ አነጋገር ፣ ወዘተ ። ይተዋወቃሉ ፡ ሊግባቡም ላይግባቡም ይችላሉ ። ጉዳዩ እሱ አይደለም ። ከጥቂት ቀናት በዋላ ፡ ካላገኘዋት ፣ እጄ ካላስገባዋት ፣ የኔ ካልሆነች ፣ ህይወቴ ካለሷ ባዶ ነው ፣ ወዘተ ማለት ይጀምራል ። እዚህ ጋር ልብ በይ እንግዲህ ። አነዚህን ነገሮች እያለ ያለው ለልጅቷ አስቦና ተጨንቆ አይደለም ፡ ለራሱ ፍላጎት እንጂ ። ስለናፈቀችው ፣ ደስ ስላለችው ፣ ስለምታምር ፣ ከሷ ጋር ከሆነ ደስተኛ እሆናለሁ ብሎ ስለሚያስብ ፣ ባጠቃላይ ልጅቷ ትሆነኛለች ብሎ እንጂ ፡ ለልጅቷ እሆናታለው ፣ ብሎ አይደለም ። አስተውይ ፡ መጀመሪያ ላይ አፈቀርኳት ብሎ ሲያወራ የሱ ህይወት ካለሷ ባዶ ሆኖ ስለተሰማው እንጂ የሷ ህይወት አሳስቦት አይደለም ። የሱ ጭንቀት እንጂ የሷ ፍላጎት አልታየውም ፤ አያውቅምም ። በቃ በዛ ሰዓት እሱ የሚፈልገው ነገር ቢኖር ልጅቷ የሱ እንድትሆን ነው ። የሱ ብቻ ። እሷ እንኳን የሌላ ሰው ሆና ማየቱ ይቅርና ሰላም እንኳን ቢሏት ካልገደልኳቸው ሊልም ይችላል ። እሷን ከራሱ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ለሴኮንድ እንኳን ማሰብ አይፈልግም ። እሷ አልፈልግህም ብትለው እንኳን በግድ ካልሆንሽ የሚል ጉድ ውስጥም ሊገባ ይችላል ። አስቢ ይሄን ሁሉ እያደረገ ያለው ለራሱ ሲል ነው ። ይሄንን ነው እንግዲህ ፍቅር ብለን የጠራነው ። እመኚኝ ግን ከዚህ ሰው በላይ እራስ ወዳድ ሰው በምድር ላይ የለም ። የፍቅር ትርጉም ግን ይህ አልነበረም ። ፍቅር ከራስ አልፎ ለሰዎች ሁሉ መኖርና መሞት ነው ። ቢተያዩም ባይተያዩም ፣ ብታምርም ባታምርም ፣ ለሱ ህይወት አስፈላጊ ሆነች አልሆነች ፣ እውነተኛ ልብ ካለው ያኔ የእውነት ፍቅር ከልቡ ይገባል ። በአይኑ ሳይሆን በልቡ ማየት ሲጀምር እሱ ሳይፈልገው ቤቱ ድረስ መጥቶለት ደጁን ያንኳኳል ። አፍቃሪ መሆን ከፈለገ ከልቧ ውጪ ምኗንም ሳያይ ፣ ምንም ሳታደርግለት ፣ ብትበድለው ብትክሰው ፣ ለሱ ሆነች አልሆነች ፣ ባጠቃላይ የሷ ነገር አሳስቦት እንጂ የሱ ጎዶሎነት ተሰምቶት አይውደድ ። ለጎዶሎው ብሎ ካፈቀረ አንድ ቀን እንዳልተሟላለት አስቦ ሊተዋት ይችላል ። የሷን ጎዶሎ ሊሞላ ቢሯሯጥ ግን አትራፊ ይሆናል ። ቅዱሱ መፅሐፍም "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" አይደል የሚለው ። ክርስቶስስ ከሰማይ ላይ ወርዶ የሰውን ስጋ የለበሰው ለራሱ ጥቅም ይመስልሻል ...? ፍቅር መጠቀም ሳይሆን መጥቀም ነው ። እውነተኛ አፍቃሪ በነገሮች ሁሉ ቅድምያ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ሰው ሰጥቶ የሚጠቅም እንጂ የራሱን ችግር ለማሸነፍ ብሎ በሌሎች የሚጠቀም አይደለም' ። ©ከወደዱት ክፍል ፴/30 ይቀጥላል ። Join us... ✦✺ @Minteno ✺✦ ✦✺ @Minteno ✺✦
Oct 31, 2020