Endet nw be slke dv 2022 memulat mclew?
Oct 28, 2020DV 2022 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን? ✅በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2022 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ ጥቅምት ሀሙስ 07/2020 ጀምሮ ህዳር 10/2020 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው። DV-2022 Program Instructions ›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች;- (በ Ethiostudents የቴሌግራም ቻናል) ↘️እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት ማለትም በ ፕሮግራሙ መሰረትም- ➡️ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቀ /ያጠናቀቀች። ወይም ➡️ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው። ↘️የ DV አሞላል ሂደቶች:- ➡️ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመቀጠልም www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት ›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ ፎርም መሙያዉ መግባት። ↘️ፎርም አሞላል‼️ 1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣ First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ። 2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ። 3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year ( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።. 4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ 5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር 6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ 7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት - የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል @Ethiostudente ➡️ በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ ፣JPEG Format መሆን አለበት። 8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት 9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ 10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል 11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት 12. What is the highest level of education you have achieved, as of today? የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ 13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር ሁኔታ መምረጥ 14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ። ↘️በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን DV-2022 ሲወጣ ማየት እንችላለን። DV-2022 Submission Confirmation : Entry success በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ የ Ethiostudents ን የቴሌግራም ቻናል ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ማረግ አይርሱ @Ethiostudente @Ethiostudente By: Maybel 👩 🎖 24 rep 16 minutes ago
Oct 28, 2020