እንዴት ናችኹ? ጥያቄዬ ለኦርቶዶክስ አማኞች ነው። እስኪ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እና በቅብዓት መካከል ያለውን ልዩነት አስረዱኝ። ቅባቶች "በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ" ይላሉ። እና እንዳንቀበላቸው ያደረገው ዋና ሐሳብ ምንድነው?
Jun 07, 2026የቃል ገንዘብስ ምንድን ነው ብንል ረቂቅነት፣ ምሉዕነት፣ ባዕልነት፣ አምላክነት፣ ክቡርነት (ቅቡዕነት) እና የመሳሰሉት ናቸው። ቃል ቅድመ ተዋሕዶም ቅቡዕ (ክቡር) ነው። አብ፣ ወልድ፣ መንፈስቅዱስ በክብር (ቅብዕ) አንድ ናቸውና። ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ማለትም ሥጋ አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይህ ደግሞ የሆነው ቅድመ ዓለም አምላክ የሆነውን ቃልን በመዋሐዱ ነው። ቃል ሥጋ ኮነ (ዮሐ. ፩፣፲፬) ባልንበት አንጻር ሥጋም ቃልን ሆነ እንላለን። የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሲሆን ለቃል የሆኑት አካላዊ ሕይወቱ መንፈስቅዱስ እና አካላዊ ልቡ አብ ለሥጋም ሆነዋል። ስለዚህ እኛ ተዋሕዶዎችና ቅባቶች የምንለያየው ለሥጋ ክብር የሆነው ማን ነው? በሚለው ነው። እኛ ቃል ስንል ቅባቶች መንፈስቅዱስ ይላሉ። ይህ ደግሞ መንፈስቅዱስ ሰው ሆነ ወደማለት የሚያመራ ታላቅ ክህደት ነው።
Jun 07, 2026