· እውነት ግን ፆታዊ ግንኙነት ምን መምሰል አለበት? አንድ ግንኙነት ያማረ እና ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉት ነገሮች አሉ 1. ግልፅነት:- ይህ ለግንኙነት መሰረት ከሚጥሉ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው ለምን? ሁለቱም ለአንድ አላማ ነው የመጡት እሱም ፍቅር ነው ምንአልባት አንዱ ወዶ ሌላው ሊርቅ ወይም ሊሸሽ ይችል ይሆናል ይህ የሚሆንበት ምክንያት ግልፅነት አለመኖር ይመስለኛል። እስኪ አስቡት እሷ እየወደደችው እሱ ግን ከእሷ በስሜት ርቆ ቢቀመጥ ምን ያህል የስሜት መጎዳት ሊገጥማት ይችላል በዚህ መሀል ሌላ እንስት ቢወድ ይህቺ ሴት ምን አይነት የስሜት መታወክ ይገጥማት ይሆን በዚህ ንግግር መሀል አንድ ታሪክ ታወሰኝ አንድ ገበሬ ነበር ይህ ገበሬ ታታሪ እና ለኑሮው ደፋ ቀና የሚል ነው እናም ክረምቱን ዘርቶ ያጨደውን ሰብል በአህያው ጭኖ ከከተማ ሊሸጥ ይፈልግና ከጎረቤቱ መጫኛ ሊዋስ ይሄዳል ይሁንና ጎረቤቶቹ የሞቀ ጨዋታ ይዘው ነበርና ከምረብሻቸው ትንሽ ቆይቼ እጠይቃቸዋለሁ በማለት ጨዋታውን ይቀላቀላል በዚህም ብዙ ደቂቃዎች ይነጉዳሉ በመሀል ግን አንድ ቀልጣፋ እና ንቁ የሆነ ገበሬ ወደ እዚያ ቤት በመግባት ሰላምታ ያቀርብና እንዲገባ ይጠይቁታል እሱ ግን አሁን እንደማይመቸውና መጫኛ ፈልጎ እንደመጣ ይነግራቸዋል በዚህም ጊዜ እንዲወስድ ይፈቅዱለታል ነገርግን ቀድሞ የመጣው ገበሬ እኔም እኮ መጫኛ ለመጠየቅ ነው የመጣሁት ብሎ ቢላቸው ቀድሞውኑ ነበር መጥኖ መደቆስ ብለው ተረቱበት ይባላል። ግልፅነትን የመሰለ ነገር የለም የዛሬውን ማንነታችንን ዋሽተን በዝምታ ብናልፈው ነገ ላይ ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል። በዚህ ጉዳይ ላይ እስኪ ምን ታስባላችሁ በዚህ ነገር ምክንያት ያጣችሁት ነገር ምንድነው እስኪ እናውራበት?
Jun 06, 2026