በትዳር ውስጥ 24 ሙሉ ዓመታትን አብረው አሳልፈዋል ድሮ ምንም በሌላቸውና በችግሩ ቀን የገዛ ወላጅ እናቱ እንኳ ሳይቀሩ በድህነቱ ጥለውትና ሰድበውት በነበረበት ጊዜ ሚስቱ ግን ገና ሳይኖራቸው በፊት የራሷን ወርቅ ለእናቱ በስጦታ ሰጥታ በፍቅር አክብራቸው ነበር። በመጡ ቁጥርም መኝታ ቤቷን ለቃ እየሰጠች፣ አብስላና ደክማ ታስተናግዳቸው ነበር። በኋላም የኩላሊት ህመም እየተሰቃየች የልጆቿን እድል ለማሳመር ቀን ከሌሊት እንደ ወንድ ደክማ ለፍታና ታትራ ዛሬ የሚታየውን ሀብትና ንብረት በሙሉ በእጆቿ ፈጠረችለት ነገር ግን በሚስቱ ደምና ላብ የቤቱ ካዝና በገንዘብ ሲሞላ ድሮ ልጃቸውን ያንቋሽሹ የነበሩት እናቱ ዛሬ በሀብቱ ምክንያት ቀረቡት ዓላማቸው ግን ያንን ሳይኖራቸው ወርቅ የሰጠቻቸውን ምራት ውለታ ረስተው የ24 ዓመቱን ትዳር ማፍረስ የታመመችውን ሚስቱንና የገዛ የልጅ ልጆቻቸውን መጥላት ሆነ እናቱ ድሮ በእሱ ላይ ያደረጉበትን በደል ረሳ አሁን በየቀኑ ለእናቱ እየደወለ የታመመች ሚስቱንና ልጆቹን ያማል ያለ ምክንያት ቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ይፈጥራል ሰላም ይነሳቸዋል ይባስ ብሎ እሷ በትግልና በህመም ያፈራችውን ንብረት ሁሉ የእኔ ብቻ ነው ንብረቴ እያለ ይፎክራል የገዛ ልጆቹንም ውርስ እየጠበቃችሁ ነው እያለ በቁማቸው ያደማቸዋል ነገሩ የባሰ የወጣው ግን ከጊዜ በኋላ ነው ባልየው አሁን እሷ ለፍታ ደክማ የሰራችውን ቤት ይሸጥ እያለ አስቸግሯታል እሷ ደግሞ ለልጆቿ ስትል በፍጹም አይሆንም በማለት እየተከራከረች ትገኛለች በዚህም የተነሳ ቤቱ የጭቅጭቅ ሆኗል ጥፋቱ የማን ይመስላችኋል ?
Jun 06, 2026በዋነኝነት የባል ! በመቀጠል የባል እናት ! የሚስት ጥፋት እናቱ እንደዛ መኾናቸውን ከመጀመሪያ ስታውቅ ኋላ አልጋ እየለቀቁ እስከማስተኛት መድረስ ሳይኾን መራቅ ነበረባት
Jun 06, 2026