ሰላም AAE በዚህ የፍቅር ሕይወቴ ላይ የበሰለ ምክራችሁን እንድትሰጡኝ ነው እና ። አሁን ላይ በጣም ወሳኝ እና "Critical Stage" ላይ ነው የምገኘው። ከፍቅረኛዬ ጋር ፍቅር የጀመርነው ገና በ2 ወራችን ነው። ነገር ግን በዚህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ80,000 ብር (80k ETB) በላይ ወጪ አድርጌባታለሁ። እሷ ገንዘብ በጣም እንደምትወድ አውቃለሁ፤ አሁን ላይ ግን ባህሪዋ በጣም አጠራጣሪ (Sus) እየሆነብኝ ነው። ይባስ ብሎ የኢንስታግራም አካውንቷን ስመለከት የምትከተላቸው (Following) ሰዎች በሙሉ ወንዶች ብቻ ናቸው። ለመሆኑ ገና በ2 ወር ውስጥ ይሄን ያህል ብር ማውጣቴ ትክክል ነው ወይስ አይደለም? እኔን በትክክል ትወደኛለች ወይስ በገንዘቤ እየተጠቀመችብኝ ነው? እየከዳችኝ (Cheating እያደረገች) መሆኑንና ታማኝነቷን በኦንላይን ወይም በራሴ መፈተን የምችልበት ምን ምርጥ ዘዴ አለ? እባካችሁ ወንድማዊና እውነተኛ ምክራችሁን ስጡኝ። አመሰግናለሁ! thank you
Jun 05, 2026የኢንስታግራም ፎሎዊንጓን ለማየት ጊዜ አታጥፋ ፌክ አካውንት ከፍተህ ከመፈተን ይልቅ ለአንድ ወር ሳንቲም ሳታወጣላት ፈትናት ከዛ እውነቱ ይወጣል
Jun 05, 2026