i am rich but lonely በቅርቡ ነው ሃብታም የሆንኩት 26 አመቴ ነው ህይወቴ ጥሩ ነው የምፈልገውን አይነት ላይፍ ስታይል እየኖርኩ ነው ግን የብቸኝነት ስሜት ይሰማኛል ቤተሰቦቼ እና ዙሪያዬ የነበሩት ሰዎች በጣም ቶክሲክ እና ክፉ ስለነበሩ ከነሱ በጣም ርቄያለሁ አንዳቸውንም ደግሜ ማየት አልፈልግም አብሮ አደግ ጓደኞቼም አብሮ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ ምቀኝነት ስለሚቀናቸው ከነሱጋርም ተቆራርጫለሁ የምኖርበት ሰፈርም ስለቀየርኩ ማንንም አላገኝም ፍቅረኛም የለኝም አሁን ላይ ፍቅረኛ የመያዝ ሃሳቡም ፍላጎቱም የለኝም ወንድ ልጅ ሰላሳው ቤት ነው ትዳር መያዝ ያለበት ብዬ ስለማስብ አሁን ላይ ፍቅረኛ ይዞ መጃጃል አልፈልግም አሁን ላይፍን ኢንጆይ ማረግ አላማዎቼን ታለንቴን አቺቭ ማረግ ነው የምፈልገው አብዛኛውን ጊዜ የብቸኝነት ስሜት የሚሰማኝ ቅዳሜ ቅዳሜ ነው 😂 የሆነ ክለብ ውስጥ የ መቶ ምናምን ሺ ብር ውስኪ አውርጄ አንዱ ጥግ ላይ ብቻዬን ተቀምጬ ለመዝናናት ስሞከር ሰዎች 3 or 4 ሆነው እየተዝናኑ በ ግሩፕ ሴቶቹም ወንዶቹም በግሩፕ መተው ሲዝናኑ ሳይ በጣም እቀናለሁ ብቸኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል ያወረድኩትን ቦትል ውስኪ ሩብ እንኳን ሳልጠጣው ትቼው እወጣለሁ ሁሌ የትም ቦታ ስሄድ ብቻዬን ነው ጓደኛማቾች ሰብሰብ ብለው ሲያወሩ ሲጫወቱ ሳይ እኔ ብቻዬን ፈላስፋ ይመስል 😭 ያው ከሰኞ እስከ አርብ ስራዬ የኦላይ ስራ ስለሆነ ከቤት አልወጣም ፎሬክስ ነው የምሰራው ከሰኞ እስከ አርብ ፈታ ብዬ ነው እቤት የማሳልፈው ከ ፎሬክሱ ውጭ የራሴ ደይሊ ሩቲን አለኝ ምናምን እና አይደብረኝም ቅዳሜ እና እሁድ ግን ለመዝናናት ስወጣ የሌለ ነው ብቸኝነት የሚሰማኝ ሰዎች ደሞ ገንዘቤን አይተው ጓደኛ እንዲሆኑኝ አልፈልግም ደሃ መስዬ ልቅረባቸው 🤔አላቅም ምን እንደማረግ 😭
Jun 04, 2026Bro negtual nika beterara tsehay endezi aynet hilm atym nightmare nw mihonbk
Jun 04, 2026