ከወንዶች ጉዳይ የቦርድ ሰብሳቢ ( ከእኔ ሚኮጵያ ) የተሰጠ መግለጫ ሴቶች ኾይ ! የቤት ኪራይ፣ የትራንስፖርት፣ የሽንኩርትና የዘይት ዋጋ ሰማይ በነካበት በዚህ ዘመን፣ “የኔ ቆንጆ፣ ዛሬ የት እንገናኝ?” ብለን ስንጠይቃችኹ ከገንዘብ በላይ የልብ ድፍረት እንዳለን ልብ በሉልን ! ! እናንተ “ለምን ቶሎ አትደውልም?” ስትሉን ፣ እኛ “ለዳታ እንሙላ ወይስ ለነገ ምሳ?” በሚል የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ እየተናጥን ሊሆን እንደሚችል ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይኽን የፋይናንስ ጀግንነታችንን ልታደንቁልን ይገባል ስል ለማሳሰብ እወዳለው ! በየቀኑ የምንሰማው ዜና፣ የዓለም ፖለቲካ ውጥረትና የሃገር መረጋጋት ማጣት እያለ፣ ይህንን ኹሉ የስነ-ልቦና ጫና ተቋቁመን “ምሳ በላሽ? ዛሬ ደግሞ ቆንጅዬ ሆነሻል!” እያለን እናንተን ለማስደሰትና ሮማንቲክ ለመሆን ስምኖክር፣ እኛ የሰላም አምባሳደሮ እንጂ ተራ ‘ጀንጃኞች' እንዳልኾንን በጭንቀት በተሞላ ዓለም ውስጥም ፍቅርን ለመዝራት የምንደክም ዲፕሎማቶች መኾናችንን አትዘንጉ ! የዶላርን ምንዛሬ ፣ የዋጋ ግሽበትን ፣ የሥራ አጥነትን ስጋት፣ እና የእናንተን Mood (ስሜት) ተለዋዋጭነትን እነዚህን ከባድ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ አደጋዎች በአንድ ላይ ተቋቁመን የምንኖር ድንቅ ፍጡሮች ነን ! ይኽን ኹሉ የሕይወትን ማዕበል አልፈን እናንተ ጋር ስንደር ቁጭ ካላችኹ ቆማችኹ ፤ ቆማችኹም ከኾነ ጥላ ወጥራችኹልን በአክብሮት ተጀንጀኑልን ! ! ዐሳብ አስተያየታችኹን በፍቅር ከታች አስቀምጡልን !
Jun 03, 2026Nigga,you have all this problem and you thinking about a way to talk or start relationship with them lol why don't you focus on winning your life rather this then you will reach here easily with out a list of reasons to get a girl
Jun 03, 2026