ሰላም ሰዎች የካቲት 14 ተመርቄ ነበር ግን እስካሁን ሥራ አላገኘሁም ሥራ ቢገኝም እንኳ ደመወዙ ለትራንስፖርትና ለመሰረታዊ ወጪዎች እንኳ የማይበቃ ነው ቤት ውስጥ መቆየት በጣም እየከበደኝ ነው ቀኔን ሳህን በማጠብ ቤት በማስተካከልና በቤት ሥራዎች እያሳለፍኩ ነው ቀንና ሌሊት እቆጥራለሁ ግን በሕይወቴ አዲስ ነገር የለም ብዬ ይሰማኛል ከጊዜ በኃላ ተስፋ እየቆረጥኩ ነው ራሴንም ቀስ በቀስ እያጣሁ እንደሆነ ይሰማኛል ከተመረቃችሁ በኋላ ይህን ዓይነት ጭንቀትና ጫና እንዴት አስተናገዳችሁት? የራሳችሁን ሥራ እንዴት ጀመራችሁ? ምን ምክር ትሰጡኛላችሁ? እባካችሁ ልምዳችሁን አካፍሉኝ 🙏💙
Jun 01, 2026Sran sra ysbal yemibalewn neger amnbetalew yehone neger mejemer arif new tnsh bihonm gebiw
Jun 01, 2026