አንዳንዴ መኖር ካለመኖር ካልተሻለ መኖር ምን ዋጋ አለው አንድ ሰው እኮ ተስፋ የሚቆርጠው ከንድ ወይም ሁለት or ሶስት አራት ግዜ ባገጠመው ነገር አይደለም ለ አስርተ አመታት እንዲያም ካለ ለ15 አመታት ብቻ ግን ከተወለዳችሁ ጀምሮ የሚያድጉ በቤተሰባችሁም ምንም የማይቀረፍ ችግር እስአመቼ ወላሂ ሰለቸኝ ነገሩ እየባሰ በቃ አይምሮየ ተጓዳ በቃ አሁን ራሴን ለማጥፋት የሆነ ድርጊት ባላደርግም ግን መሞት እፈልጋለሁ የመኖር ተስፋ የለኝም 21አመት ሊሞላኝ ነው አሁን በቃ በትንሹም በትልቁም ለቅሶ መፍትሄ ይሆናል ሰዎች ዝቅ አርገው ሲያያችሁ በቃ ጠቅሼ የማልጨርሰው situation ራሴን ሰላም ለመስጠት ወዴት ልሂድ
May 25, 2026አሰላም አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ። የልብሽን ጭንቀት፣ የውስጥሽን ስብራት እና የደረሰብሽን ፈተና እንደ አንድ ወንድምሽ ተረድቼዋለሁ። ቃላትሽ ልብን ያደማሉ፣ ነገር ግን እህቴ ሆይ፣ ይህንን ስሜትሽንም እንድትገልጪ አላህ የፈቀደልሽ ገና የሚወድሽና ተስፋ እንድትቆርጪ የማይፈልግ ባሪያው ስለሆንሽ ነው። ዛሬ የምታዩት ጨለማ፣ ነገ በአላህ ፈቃድ በእርግጠኝነት ይገፈፋል። እህቴ፣ ይህች አለም የፈተና ቤት ናት። አላህ እንዲህ ይላል፡- "በመፍራት፣ በረሃብም፣ በገንዘቦች፣ በነፍሶች፣ በፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንፈትናችኋለን። ታጋሾችንም (በጀነት) አብስር።" (አል-በቀራህ፡ 155)። ከአንቺ በፊት የነበሩት ነብያትና የአላህ ወዳጆች ከዚህ በላይ ፈተና ደርሶባቸዋል።
May 25, 2026(edited)