አይገርምም ? ? መንግሥታትና ባንኮች ከምንም ተነስተው ወረቀት እያተሙ ፤ "ይህ ዋጋ አለው" ብለው ሕግ ሲያወጡና እኛም ያንን ወረቀት ለማግኘት ሕይወታችንንና ጉልበታችንን ስንሸጥ ? በወረቀት በታሸገ በተስፋ ባርነት ስንኖር ? አይደንቅም ? ? ትላንት ለምነው የባንክ አካውት ሲያስከፍቱህ የነበሩ ተቋማት በድንገት ተነስተው ያስቀመጥከውን የገዛ ገንዘብኽን ከዚኽ በላይ አንሰጥኽም ከማለት አልፈው በማንአለብኝነት እንዲኽ ካላደረክ በማለት አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ አስገብተውኽ አካውንትኽን ሲዘጉት ? አዎ " ለአምጪው እንዲከፈል ሕግ ያስገድዳል " በዚኽ - ግዴታ - አለ ! ! አያስገርምም ? ማኅበራዊ ሚዲያው ትንሹም ትልቁም " ይዘኽ ተገኝ " " ገንዘን ይኑርኽ " " ዋናው ገንዘብ ነው " እያለ ሲደሰኩርና ሴትን ( ሰውን ) ለማግኘት ፤ ለመከበር ገንዘብን ተቀዳሚ ሲያደርገው አያስደነግጥም ? " ንሕነሰ ወለጥነ ሥርዓቱ ለእግዚአብሔር "
May 22, 2026so what do you suggest? do you have a better modern society functioning system idea?
May 22, 2026