አይኔን በማይበት ወቅት እንደ ትናንሽ ነጥቦች፣ የሸረሪት ድር ወይም ጠማማ ክሮች ሚመስሉ ነገር ይታየኛል • ዓይኔን ወደ ግራና ቀኝ ሳታንቀሳቅስ አብረው ይንቀሳቀሳሉ። • በተለይ ደማቅ ብርሃን፣ ነጭ ግድግዳ ወይም ወደ ሰማይ ሳይ ጎልተው ይታዩኛል ግን ምንም የህመም ስሜት የለኝም የአይን ሀኪም ጋር ታይቻለሁ ምንም የለም ።የደም ምርመራ አድርጌያለሁ እና የvatamin b12 175 ነው ብሎ መድሀኒት አዘዘልኝ በምላስ ስር በማድረግ ነው የሚወሰደው በ ሳምንት 1ጊዜ ለ 3ወር እና ከጀመርኩት 3ሳምንት ሆኖኛል ምንም ለውጥ የለውም ጭራሽ ሰዉነቴን ድንዝዝ እያለኝ ነው ሌላ ምን አይነት ምርመራ ማድረግ እችላለሁ? በጣም ጨንቆኛል አሁን ጥላዎች እየበዙ ነው አመሰግናለሁ 🙏
May 21, 2026እንዴ እኔ አይደለሁም አይደል ፖስት ያደረኩት 😳😳 የምር አይኔ ላይ ሰሞኑን ከሁለት ሳምንታት በፊት ያስተዋልኩትን ምንም ሳትጨምር ሳትቀንስ ነው የፃፍከው። ሁሉም የገለፅካቸው ጠማማ ክሮች ትቁር ነጥቦች ወደጎን አይኔን ሳንቀሳቅስ አብረው ይንቀሳቀሳሉ። እና የእኔ የግራ አይኔ ላይ ብቻ ነው እና ትንሽ በዥ ይልብኛልም እንደ ቀኙ አይኔ ጥርት አድርጎ አያይም። በጣም እያስጨነቀኝ ነው። ምን ተሻለን ብሮዬ እኔ አልታየሁትም በርግጥ።
May 21, 2026