ሠላም ሰዎች፣ እኔምለው እስኪ ክፋ ሰዎች እንዴት ነው ክፋ የሆናችሁት ንገሩኝ እራስ ወዳድነትት የሚመጣው እንዴት ነው ? እኔ እየገፋኝ እየበደሉኝ ፈገግ ብዬ እሄዳለሁ ደሞ ቂም አልይዝ አልማር መልሼ ደሞ ሌላ ሰው እረዳለሁ አጉል መካሪ አስተማሪ አስተማሪ ያጫውተኛል አጉል ቄስ መነኩሴ ልሁን ባይም ነኝ አጉል አጓጉል ጠቢቡ ሠለሞንንም ያጫውተኛል ! ሰው የሚጠቅመውን አይወድ እኔ ለሰው ሟች ሰው ለኔ ቢላ እንደሳለ እግዚአብሔር ባይጠብቀኝ ድሮ ነበረ የሞትኩት ! የብዙ ልጆች ህይወት ወደ ጥሩ እድገት እንዲቀየር ትልልቅ አስተዋፅኦ አድሮጌ ፍሬ አይቼባቸዋለሁ ሰው ግን ዞሮ ለኔ ጦር ይመዛል! እግዚአብሔር ጦሩን ጨርቅ ቀስቱን ገመድ አድርጎ ያሳልፈኛል አሁን አሁን ግን በክፋ ሰዎች ቀናሁ ሰው ቢሞት ቢሰቀል ዞሮ ለማይመለከትህ ሰው ማዘን ነገ ሲያልፍለት በመኪና እላይህ ላይ ካላለፍኩብህ ሲል ያሳዝናል! ሰውንስ ቢመጣ ቢሄድ አይሞቀኝ አይበርደኝ ብቻ ሰውን በወደድኩበት ልክ እራሴን ብወድ እላለሁ መሆን ግን አልቻልኩም!
May 18, 2026“በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤” — መዝሙር 37፥1
May 18, 2026