For my orthodox people why don't we eat pork or animals shekonaw kift yalhonut yemntewew......i thought was in blukidan since paul said to eat everything unless yemaismamchun kalhone besteker ena demo we are the only one who don't eat the coptics orthodox eat too leza nw.......thank you
May 16, 2026መጽሐፍ ቅዱስ በሐዲስ ኪዳን የከለከላቸው ምግቦች በዋናነት ሦስት ናቸው። እነዚህም ሞቶ የተገኘን መብላት እንደማይገባ፣ ደምን ወይም ጥሬ ሥጋን መብላት እንደማይገባ፣ ለጣዖት የታረደን መብላት እንደማይገባ ናቸው። "ዳዕሙ አዝዝዎሙ ይርሐቁ እምዘይዘብሑ ለአማልክት ወእማውታ ወደም" እንዲል (የሐዋ. ሥራ 15፥20)። ይህንን ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 23ም ገልጾታል። ከዚህ ውጭ ያሉትን ግን የሚበላ አመስግኖ መብላት፣ የሚጠጣም አመስግኖ መጠጣት ይገባዋል። የሚጠጣ የማይጠጣውን፣ የማይጠጣ የሚጠጣውን ሊነቅፈው አይገባም። "የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ። እግዚአብሔር ተቀብሎታልና" እንዲል (ሮሜ 14፥3)።
May 16, 2026