ከሰሞኑ በብዙ እኅቶች ዘንድ እያስተዋልኩት ከነበረው በመነሳት ትዳር አያስፈልግም የሚሉት ምን አይነት ሴቶችና ምን አይነት ምክንያት ያላቸው ናቸው የሚለውን ስመረምረው ትዳርን መጥላት መብት ኾኖ ሳለ :- ድንግልና ወይም መንፈሳዊ ጥሪ በሌለበት ሁኔታ ትዳርን የሚጠየፉ ሴቶች፣ ብዙውን ጊዜ የሚሸሹት ትዳርን ሳይሆን "ለአንድ ሰው ታማኝ የመሆንን" ከባድ ኃላፊትና ዋጋ ነው። መንፈሳዊ ዓላማ ሳይኖራቸውና ንፅህናን ሳይጠብቁ፣ ትዳር አያስፈልግም የሚሉት ሴቶች ትዳርን ጠል የኾኑበት ምክንያት ትዳር የሚጠይቀውን 'ዲሲፕሊን' የማያሟሉና ለሟሟላትም ( ራሳቸውን ለማብቃት ) ጥረት የማያደረጉ ድኩማን ናቸው ! እነዚህ ሴቶች የአንድ ሰው ሚስት መሆንን "እስር ቤት" ብለው እየጠሩ፣ የብዙዎች "የመጫወቻ ሜዳ" መሆንን ግን "ነፃነት" የሚሉ ናቸው ! ታዲያ እነዚህ ሴቶች በትዳር ውስጥ የሚገኙ ልጆችንና ቤተሰባዊውን ድባብ እያደነቁ ያንን ድባብ የሚፈጥረውን (ትዳርን) በመጥላት፣ ዛፉን ቆርጠው ፍሬውን የሚጠባበቁና ዛሬ ላይ ነገአቸውን የሚሰርቁ ናቸው ። ታዲያ እነዚህ ሴቶች ወንድ አያስፈልገኝም፣ እራሴን ችያለሁ በሚል መፈክር ኖረው ሰላሳዎቹ አጋማሽ ላይ ሲደርሱና ጓደኞቻቸው ሁሉ አግብተውና ወልደው ሲመለከቱ ፣ "ጥሩ ወንድ ጠፋ" የሚል የለቅሶ ዜማን የሚያዜሙ ናቸው። ካለፈው የፍቅር ግንኙነታቸው የተጎዱም የዚኽ ዜማ አቀንቃኝ ናቸው። ( እነዚኽ የስነ ልቦና ድጋፍ ያሻቸዋል ) ! እና :- አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ታማኝ መሆንን (ትዳርን) እንደ እስር ቆጥራ፣ ነገር ግን በየጊዜው ለተለያዩ ወንዶች ስሜታዊ እና አካላዊ ተገዢ መሆንን ነፃነት ካለች፤ ነፃነቱ ያለው ምርጫው ላይ ነው ወይስ ድርጊቱ ላይ? ወይንስ 'ነፃነት' የሚለው ቃል ኃላፊነትን ላለመሸከም የምንጠቀምበት ጭንብል ነው?
May 14, 2026Ahun yalenew ayenet setoch lenoru yechelal gn dmo yewndochus ke and and wendoch Ga tear malet Eko bensesa sratena mehon malet nw imagen megebu sereta lebesun ateba betun ket arga yeza enzi Hulu setatena ketro meyawtaawn wechi kerelet malet Adelm kezabegebim kesu ekul sereta gebim eyametach Lij semata ket arga yelj halafinet wesda esu yetm kemanm Ga Adel ende menzelazelew bealetedar honao menzelazelew wnd snt nw eski weteh researched sera mestun bet asekemeto yet wetash gebash eye ende felege
May 15, 2026