I had an accident at work 3months ago and eskahun demoz eyekefelug neber sra salgeba sickleav eyasgebaw malet new ena kemiketlew jemro anasgebam alig is this legal and mn yahl gize new mekfel yalebachew
May 11, 2026በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ በሚሸፈን አሰሪ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ፣ በስራው ላይ ጉዳት ቢደርስበት አሰሪው 1ኛ/ ጉዳት ለደረሰበት ሠራተኛ የመጀመሪያ ሕክምና ዕርዳታ በጊዜው መስጠት አለበት፣ 2ኛ/ ጉዳት የደረሰበትን ሠራተኛ ተስማሚ በሆነ የመጓጓዣ ዘዴ በአቅራቢያው ወደሚገኘው የሕክምና ጣቢያ ማድረስ አለበት፣ 3ኛ/ አሰሪው የህክምና ወጪዎችን ማለትም የጠቅላላና የልዩ ሕክምና እንዲሁም የቀዶ ሕክምና ወጪዎች፣ የሆስፒታልና የመድሃኒት ወጪዎች፣ የማንኛውም አስፈላጊ ሰው ሰራሽ ምትክ ወይም ተጨማሪ አካሎችና የአጥንት ጥገና ወጪዎችን የመሸፈን ግዴታ አለበት።
May 11, 2026