ወገንታት ህዝበታት እንዴት ናቹ? so ወደ ገደለው ስገባ ከዛሬ 2 አመት ከ 7 ወር በፊት ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር በነበርንበት ሰዐት ቃል ገብቼላት ነበር 1 አመት ብቻ ስጪኝ እና ሁሉንም ነገር አስተካክላለሁ (ገንዘብ) እና ይሄን ሀሳብ እሷም ተቀበለቺኝ እኔም አንገቴን ድፍቼ እግሬን ቆልፌ መስራት ጀመርኩኝ እቅድቻን እና የኔ ቃል የነበረው ከ 2 አመት ቧሀላ ከፍቅረኛ አልፈን ለትዳር ነበር እና በሆነ አጋጣሚ በማላውቀው ምክንያት ዝም አለቺኝ ስልኬን አታነሳም ሙሉ በሙሉ ignore ገጨቺኝ በጓደኞቿ ለመጠየቅ ስሞክር እንደማትፈልገኝ አይነት ነገር ነው ንግግሯ በrecord ሲያሰሙኝ እና በቃ መለማመጤን ተውኩና ስራዬ ላይ ብቻ focus አረኩ እሷን አሁንም ድረስ አፈቅራታለሁ እና ቃሌን ማክበሬን እንድታውቅልኝ በጣም ከልቤ እፈልጋለሁ አውቃለሁ የ Ego ፀባይ እንደሆነ ግን የኔ ፅናት እና ማንነት የት ድረስ እንደሆነ እንድታውቅልኝ እፈልጋለሁ ከኔ ቧሀላ ፍቅረኛ እንደያዘች አውቃለሁ ግን ልጁ ከኔጋ ሚወዳደር ራሱ አልነበረም even የሆነ ጊዜ ሰላም ብሎኝ ያውቃል አንተ ነህ አይደል የ... ጓደኛ ብሎ ሞቅ አርጎ ሰላም አለኝና ጓደኛዬ ነው ብላው? ለሳምንት የዋዠቀ ጥያቄ ውስጥ ነበርኩ ይባስ ብሎ እኔን የተወቺኝ ለሱ ነበር ምን ቢኖረው ነው ብዬ ስጠይቅ የሀብታም ልጅ ነው ሀብታም አይደሉም ግን like እንደኔ ያጣ የነጣ የገረጣ አልነበረም ግን ይከነክነኛል ለምን የሚል ገንዘብ ወዳድ እንደሆነች ገብቶኛል so ይሄን ነገር በምን ላረጋግጥላለት የኔን አቅም አሁን ንብረቴንም ገንዘቤንም ጨምሮ 11.8M አለኝ ቲማቲም እና ሽንኩርት ማሳ አለኝ so እንዴት አድርጌ ልበቀላት በሷ እልህ ነው ራሱ ፍቅረኛ ሳልይዝ መዝናናት እያማረኝ ስራና ስራ ብቻ ብዬ ስሰራ የነበረው ምን ትላላችሁ???
May 08, 2026አመስግናት እንጂ የትኛውም ሞቲቬሽናል ስፒች እና ፖድካስት ላይ የማታገኘውን ለውጥ እኮ ነው የሰጠችህ
May 08, 2026