ከሰው ጋር አብሮ ለመኖር መተዋወቅ ወይስ አለመተዋወቅ??? ሳታውቁት ለመኖር ይከብዳል ደሞ በደንብ ስታውቁት የዛ ሰው ክፋቱ ተንኮሉ ምናምን ይገለጥላችሁአል.... So የትኛው የተሻለ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ???
May 04, 2026ሰውን ስላወቅከው ወይም ስላላወቅከው ሚቀየር ማንነት የለውም። ስለዚህ ነገር በማሰብ አትድከም። ሁሌም ለሰው ቀና አመለካከት ይኑርህ እና ስለራስህ ለሰው አብዝቶ ከመናገር ተቆጠብ። መቀራረብ መልካም ነው ነገር ስለእርሱ እንድታውቅ ከሚፈቅድልህ በላይ ለማወቅ አትድከም ዝም ብለህ የራስህ ሕይወት ላይ አተኩር። ሚስጥራዊ እና ቁጥብ መሆን በሰው ዘንድ ተወዳጅ ያደርግሀል።ስላንተ ብዙ ሚያውቀው ነገር ከሌለ እንዴት አርጎ ሊጠላህ ይችላል?..ሌላው ደግሞ ሰው እንዲወድህ ወይም እንዲያከብርህ ብለህ አንዳች ነገር ከማድረግ ተቆጠብ።ሁሌም ፈጣሪን ሚያስደስት ነገር ማድረግ ላይ እና እርሱ ሚወደው ስብዕና እንዲኖርህ መጣር ተገቢ ነው። ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ ማዘውተር መልካም ነው። ጥያቄህን በተረዳሁት መልክ ነው የመለስኩልህ ምናልባት ማይገናኝ ነገር ተናግሬ ከሆነም ይቅርታ እጠይቃለሁ።
May 04, 2026