ሰላም ሰዎች ፍቅረኛ አለኝ 3 አመት አለፈን በአብሮነት በጣም እንዋደዳለን እንተሳሰባለን ሃይማኖታችንን ግን የተለያየ ነው እግዚአብሔር ያዉቃል ብለን አለን እስካሁን ጥያቄዬ ይሄ አደለም ፍቅረኛዬ የራሱ ስልክ ቤት አለዉ መጀመሪያ ተቀጥሮ ነበር ሚሰራዉ በኃላ ተበዳድሮ ምናምን የራሱን ከፈተ የራሱን ስራ ከጀመረ ወዲህ ግን በቃ ስራዉም ቀዘቀዘ ገቢም የለዉም ብዙም እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስንገናኝ የምሳ ምናምን እኔ ነኝ ምከፍለዉ አንዳንዴም ብር እሰጠዋለሁ ሱስ ምናምን የለበትም ለስራ ነዉ ሚያዉለዉ በፊት ምንም አይመስለኝም ነበር ሲደጋገም ግን እየደበረኝ መጣ እስከመቼ ነዉ እንዲህ ምዘልቀዉ ብዬ አስባለሁ ብር ሲያወጣ እስቀቃለሁ በእዉነት በዛ ላይ ነገ የኔ ይሁን አይሁን ለማላቀዉ ሰዉ ለምንድነው ይሄ ሁላ ዋጋ ምከፍለዉ ብዬ አስባለሁ እስከመቼ ያልፍልናል ብዬ ታግሼ ልቆይ እየከበደኝ ነዉ ራሴ ተቸግሬ ሌላ ችግር ምን ላርግ አትፍረዱብኝ ሁለት አመት ጠብቄያለሁ ጥሩ ነገር ይመጣል ብዬ ግን ደከመኝ በእዉነት መፍትሄ ሳጣ ነዉ የመጣሁት ምክራቹን ስጡኝ
May 03, 2026አብራችኹ 3ዓመት ሆኗችኹ ነገ የእኔ ይኹን አይኹን የማላውቀው ሰው ሰትይ ምን ማለት ነው ሲያልፍለት ይተወኛል ብለሽ ነው ወይስ በዚኽ ችግሩ ከቀጠለ አብሬው አልቀጥልም የሚል ስጋት እንዲኽ ያስባለሽ ? እየውልሽ ልጁ ሥራው ካላዋጣው ሌላ አማራጭ ይፈለግ ወይም ሥራው አዋጭ የሚያደርግበትን መንገድ በጋራ ፈልጉ ! የሥራ ቦታ መቀየር ሊኾን ይችላል ከሥራው ጋር ጎን ለጎን አብሮ ሊሠራ የሚችል ነገር መጀመር ሊኾን ይችላል እንደዛ አይነት አማራጭ ፈልጉ! በእነዚኽ አይነት ዐሳቦች ካልተስማማ ቢያንስ ገንዘብ ላለመስጥ ወይም ለመለያየት ምክንያት ታገኛለሽ። ከቀድሞ መሰረታዊው ጉዳይ የኾነው ሃይማኖት ያላሳሰባችኹና እግዚአብሔር ያውቃል ብላችኹ የተግማማችኹ (ለቃሉ ይቅርታ) ሰዎች አኹን ገንዘብ ሲኾን እግዚአብሔር ያውቃል እንዳትሉ ምን አገዳችኹ🙄
May 03, 2026(edited)