እንዲኽ አይነት ዜናዎችን ስትመለከቱ ምንድነው የሚሰማችኹ ? እንባ እንባ አይላችኹም ? ውስጣችኹ ቁጭት አይፈጠርም ? ሃገራችን ፍትሕ ርትዕ እንዲሰፍንባት ምን ላድርግ አትሉም ? በየቤተ እምነቱ ያለ የገንዘብ ምዝበራ አያንገበግባችኹም ? የቀኖናው ጥሰት አያቃጥላችኹም ? እሺ ምንም ማድረግ ባንችል ቢያንስ ግን "ለምን" "እንዴት" ብሎ የሚጠይቅን ሰው ለምን በደቦ መቀጥቀጥ ይቀናናል ? የወደድነው ያገነንነው ሰው ሲጠየቅ ሲመረመር ጠያቂውን መስደብ ማንጓጠጥ ለምን ይቀድመናል ? ሀብታም ሀገር እያለን በድህነት እንድንኖር የፈረዱብንን የቤተ መንግሥትን የቤተክህነትን የሚዲያ ሰዎችን ማንቆለጳጰስ እስከ መቼ ነው ? ሀገራችን ዛሬ " ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ነጽር ግፍዕየ ዘይገብሩ በላዕሌየ " እያለች ትጮሃለች ! ! ! ምንም ማድረግ ካልቻላችኹ ቢያንስ ተቆጩ እረሩ ! ! የሚጠይቀውንም ሰው ለመቃወም አትቸኩሉ " አንዳንዴ የምንጠይቀው መልስ ስለምናገኝ ሳይኾን ፍቅር አስገድዶን ነው ! መጠየቅ ባትችሉ ቢያንስ ለማመስገንም ኾነ የእውቅና ማማ ላይ ለመስቀል አትቸኩሉ ! ! ደግሞም " አትፍረድ " የሚል ኀጢአትን መሰወሪያ ቃል አትጠቀሙ ! ጌታ በቅን አትፈርዱምን ? ሲለን ጳውሎስም በውስጥ ባሉት ላይ እናንተ አትፈርዱምን ? ሲል ይጠይቀናል ! ዛሬ ሥጋዊ ኦዲተርና በዚኽ መልክ መዘረፏን የሚገልጽ የጋዜጣ እትም የሌላትን ቤተክርስቲያን በገንዘባችኹ አታጥፏት ( ኦርቶዶክሳዊያን )
May 03, 2026